የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በፕሪምየር ሊጉ በአንደኛ ሳምንት ጅማ አባጅፋር ከ ሀዋሳ ከተማ በመደረጉት ጨዋታ በተከሰተው የስፖርታዊ ጨዋነት ጥሰት ጅማ አባ ጅፋርን 150 ሺህ ብር እና ሁለት የሜዳው ጨዋታዎችን ከከተማው 150 ኪሎሜትር ርቀት እንዲያደርግ ቅጣት ማስተላለፉ ይታወሳል።
ጅማ አባ ጅፋር በ5ኛው ሳምንት ሲዳማ ቡናን የሚያስተናግድ ሲሆን የቅጣቱ ተግባራዊነትም በዚህ ጨዋታ ተግባራዊ እንደሚያደርግ ታውቋል። በዚህም መሰረት እሁድ 09:00 ጅማ ስታድየም ላይ ሊደረግ የነበረው ጨዋታ ወደ ሰኞ ህዳር 25 ሲሸጋገር ቦታውም አዳማ አበበ ቢቂላ እንዲሆን ተወስኗል። የይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ ቅጣቱን ወደ አንድ ጨዋታ ዝቅ በማድረጉ በ7ኛ ሳምንት ከኢትዮጵያ ቡና ጋር በሜዳው የሚያደርገውን ጨዋታ በጅማ ስታድየም የሚያካሒድ ይሆናል፡፡
ጅማ አባ ጅፋር እና ሲዳማ ቡና ከ 4 ጨዋታዎች 3 ነጥብ በመያዝ 13ኛ እና 14ኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።