ዛሬ እየተደረገ ባለው የሼር ካምፓኒው ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ፕሪምየር ሊጉ እንደሚመለስ የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት ገልጸዋል፡፡
የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አክሲዮን ማኅበር ዛሬ ለሁለት ቀናት የሚቆይ ስብሰባ እያደረገ ይገኛል፡፡ በዛሬው የውይይት መድረክ ላይ የኢፌዲሪ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ኤልያስ ሽኩር፣ የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳይያስ ጂራ እና የአክሲዮን ማኅበሩ የቦርድ ሰብሳቢ መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ የመክፈቻ ንግግር በየተራ አድርገዋል። በተለይ አቶ ኢሳይያስ እንዲህ ሲሉ ተናግረዋል። “የዚህ ውይይት ተሳታፊዎች ሁላችሁም እንኳን ደስ አላችሁ። ባለፉት ወራት ከመንግሥት አካላት በሚገባ ስንነጋገር ቆይተናል። ሆኖም ውድድሮች ወደ የቦታቸው መመለስ ስላለባቸው ከመንግሥትም ውድድራችን በጥንቃቄ እንድናካሂድ ፍቃድ አግኝተናል።” ብለዋል፡፡
የዛሬው የአክሱዮን ማኅበሩ ጠቅላላ ጉባዔ ውሎ ለሚዲያ አካላት ዝግ የተደረገ ቢሆንም ሶከር ኢትዮጵያ በስብሰባው የተነሱ ነጥቦች ዙርያ ያሉ መረጃዎች ሲደርሳት ለእናንተ የምታቀርብ ይሆናል፡፡
© ሶከር ኢትዮጵያ
👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም
👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ
👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!