ክለቦች የቅድመ ውድድር ዝግጅት ማከናወን ሊጀምሩ ነው

ለ2013 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የውድድር ዘመን ክለቦች የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን ሊጀምሩ ተሰናድተዋል፡፡

የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ወደ ሀገራችን ከገባ ጊዜ አንስቶ በሀገራችን ሲደረጉ የነበሩ እግር ኳሳዊ ውድድሮች ሙሉ በሙሉ በመጋቢት ወር አጋማሽ 2012 ጀምሮ መሰረዛቸው ይታወቃል፡፡ ከስድስት ወራት በላይ ተዘግቶ የቆየው ውድድር በድጋሚ በቅርቡ እንደሚመለስ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳይያስ ጅራ በዛሬው ዕለት ለኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ክለቦች ማብሰራቸው የሚታወቅ ሲሆን ክለቦችም ለ2013 የፕሪምየር ሊግ ውድድር ይረዳቸው ዘንድ በቅርብ ቀናት ወደ ቅድመ ውድድር ዝግጅት ሊገቡ እቅድ መያዛቸውን ሶከር ኢትዮጵያ ያገኘችው መረጃ ይጠቁማል፡፡ ስድስት የሚሆኑ የሊጉ ክለቦችም ከመስከረም 20 በኃላ ባሉ ቀናት ዝግጅት ለማድረግ እንደሚገቡ ሰምተናል፡፡

የሊግ ኩባንያው ምናልባትም ነገ የፕሪምየር ሊጉን ማስጀመሪያ ቀን ይፋ የሚያደርግ ከሆነ ክለቦች ወደ ዝግጅት ሲገቡ ምን አይነት ጥንቃቄ ሊከተሉ እንደሚገባ መመሪያ እንደሚሰጣቸው ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!