መቐለ 70 እንደርታ ከተከላካዩ ጋር ተለያይቷል

ከአራት ዓመታት ቆይታ በኋላ ከመቐለ 70 እንደርታ ጋር የተለያየው አሌክስ ተሰማ ቀጣይ ማረፍያው በቅርቡ ይታወቃል።

ባለፉት ሦስት ዓመታት በዋናው ሊግ ደረጃ በወጥነት ጥሩ ብቃት ካሳዩት የመሐል ተከላካዮች አንዱ የሆነው አሌክስ ተሰማ የዳሽን ቢራ መፍረስ ተከትሎ በወቅቱ የከፍተኛ ሊግ ተወዳዳሪ ለነበረው መቐለ በ2009 ፈርሞ በዛው ዓመት ቡድኑ ወደ ፕሪምየር ሊግ እንድያድግ ሚና የነበረው ሲሆን በ2011 ቡድኑ የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ ሲያነሳም ትልቅ ሚና ከነበራቸው ተጫዋቾች አንዱ ነው።

ተጫዋቹ ከአራት ዓመታት የመቐለ ቆይታ በኃላ ከክለቡ ጋር ተለያይቶ በቅርቡ ወደ ሌላ ክለብ ለመቀላቀል ተቃርቧል። በቀጣይ ማረፍያው ዙርያ ከሶከር ኢትዮጵያ ቆይታ የነበረው አሌክስ ከአንድ የሊጉ ክለብ ጋር ከስምምነት ለመድረስ ከጫፍ እንደደረሰ ገልጾ ከመቐለ ጋር ባሳለፋቸው ዓመታት የክለቡ ደጋፊዎች ላሳዩት ድጋፍ እና አክብሮት አመስግኗል።

” ባልጠበቅኩት መንገድ ከምወደው ክለብ ጋር ለመለያየት ችያለው። ሆኖም በክለቡ ቆይታዬ ደጋፊዎች ላደረጉልኝ የማያቋርጥ ድጋፍ እና አክብሮት ከልብ አመሰግናለሁ። በቀጣይ ቀናትም ወደ ሌላ ክለብ ለመዘዋወር ከጫፍ ደርሻለው።”

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!