የአማካይ ሥፍራ ተጫዋቹ ዮሴፍ ዮሐንስ በሲዳማ ቡና ውሉን አድሷል፡፡
የ2013 ቅድመ ዝግጅታቸውን ከጥቅምት 5 ጀምሮ ለመጀመር በእቅድ ላይ የሚገኙት ሲዳማ ቡናዎች በርካታ አዳዲስ እና ነባር ተጫዋቾች ባለፉትን ሳምንታት ሲያስፈርም ቆይቶ የአዳዲስም ሆነ የነባር ተጫዋቾችን ኮንትራት የማስፈረም ሒደቱን አገባዷል፡፡ ወሠሉ መጠናቀቁን ተከትሎ ከሌሎች ክለቦች ጋር ስሙ የተያያዘው የተከላካይ አማካዩ ዮሴፍ ዮሐንስ በመጨረሻም በክለቡ ለተጨማሪ ሁለት ዓመት ኮንትራት ፈርሟል፡፡
ዮሴፍ ከሀዋሳ ታዳጊ ቡድን ከተገኘ በኋላ ወደ ሀላባ ከተማ አምርቶ መጫወት የቻለ ሲሆን ያለፉትን አራት ዓመታት በሲዳማ ቡና ጥሩ ቆይታ አድርጓል፡፡ በተለይ ከ2011 ጀምሮ በክለቡ መልካም እንቅስቃሴን ሲያደርግ የነበረው ይህ ተጫዋች ዘንድሮ በአሰልጣኝ ዘርዓይ ሙሉ ስብስብ ውስጥ የምንመለከተው ይሆናል፡፡
© ሶከር ኢትዮጵያ
👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም
👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ
👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!