ከፍተኛ ሊግ | አቃቂ ቃሊቲ ዝውውሩን ተቀላቅሏል

አቃቂ ቃሊቲ ክፍለከተማ ቡድን ሦስት አዳዲስ ተጫዋቾችን አስፈርሟል፡፡

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ምድብ ሀ ተሳታፊ የሆነው አቃቂ ቃሊቲ ክፍለከተማ ከአንደኛ ሊግ እስከ ከፍተኛ ሊግ ድረስ ሲያሰለጥን ከነበረው አሰልጣኝ ፀጋዬ ወንድሙ ጋር ከተለያየ በኋላ የአሰልጣኝ ቅጥር ማስታወቂያን አውጥቶ ሲያወዳድር ቆይቶ ከቀናት በፊት አሰልጣኝ ዳዊት ታደለን ዋና አሰልጣኝ አድርጎ ከቀጠረ በኃላ ወደ ዝውውሩ ገብቷል፡፡ በዚህም መሠረት አንተነህ አየለ (ተከላካይ ከገላን ከተማ)፣ ዮናታን አብዩ (ተከላካይ ከገላን ከተማ) እና ሱራፌል አየለ (አጥቂ ከባቱ ከተማ) አዳዲስ ተጫዋቾች አድርጎ አስፈርሟቸዋል፡፡ በቀጣዮቹ ቀናትም ክለቡ የአዳዲስ እና ነባር ተጫዋቾችን ያስፈርማል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉ሳንዘናጋ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!