የከፍተኛ ሊግ የምድብ ሀ ተወዳዳሪው ወልዲያ ከተማ ስድስት አዳዲስ ፈራሚዎችን ወደ ስብስቡ ቀላቅሏል፡፡
ከፈራሚዎቹ መሀል በፕሪምየር ሊጉ በደደቢት፣ ጅማ አባ ቡና፣ ወልዋሎ እና አዳማ ከተማ እንዲሁም በኢትዮጵያ ቡና ተጫውቶ ያሳለፈው አማካዩ ሄኖክ ካሳሁን፣ በአርባምንጭ ከተማ እና ሀምበሪቾ ዱራሜ ሲጫወት የምናውቀው ሌላኛው አማካይ ቴዲ ታደሰን ጨምሮ ዳዊት ደጋአረገ (ተከላካይ ከደደቢት)፣ ኪዳኔ ተስፋዬ )ተከላካይ ከመድን)፣ ዮሀንስ ኪሮስ (አጥቂ ከጌዲኦ ዲላ) እና ቀፀላ ፍቅረማርያም (አጥቂ ከአዲስ አበባ ከተማ) ክለቡን የተቀላቀሉ አዳዲሶቹ ተጫዋቾች ሆነዋል፡፡
©ሶከር ኢትዮጵያ