በከፍተኛ ሊጉ ተወዳዳሪ የሆነው ወላይታ ሶዶ ከተማ የአሰልጣኝ እና ረዳቱን ውል ያራዘመ ሲሆን ስምንት አዳዲስ ተጫዋቾችንም አስፈረመ፡፡
በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ምድብ ለ ላይ ተወዳዳሪ ከሆኑ ክለቦች መካከል አንዱ የሆነው የወላይታ ሶዶ ከተማ ለዘንድሮው ዓመት የሊጉ ተሳትፎው ተጠናክሮ ለመቅረብ የአሰልጣኝ ሀብተማርያም ጳውሎስ እና የረዳት አሰልጣኙን ኮንትራት ያራዘመ ሲሆን ለቡድኑ ይሆናሉ ያላቸውን አዳዲስ ስምንት ተጫዋቾችንም አስፈርሟል፡፡
ኤልያስ ዘአማኑኤል (ግብ ጠባቂ ከአክሱም)፣ በእርሱፍቃድ ተፈራ (ከወላይታ ድቻ ግብ ጠባቂ)፣ ብሩክ ዓባይነህ (አማካይ ከቂርቆስ) ሰለሞን ጌታቸው (አማካይ ከኢኮሥኮ)፣ ኃይለየሱስ ኃይሌ (አጥቂ ከቤንች ማጂ ቡና)፣ ምስክር መለሰ (ከድቻ U20 አማካይ)፣ በረከት ተሾመ (ከአረካ ከተማ አማካይ)፣ ሙሉቀን ተስፋዬ (አማካይ ከአረካ ከተማ) አዲሶቹ የክለቡ ፈራሚዎች ናቸው፡፡
©ሶከር ኢትዮጵያ