ቅዱስ ጊዮርጊስ የጀርመናዊውን አሰልጣኝ የልቀቁኝ ጥያቅ ተቀብሎ ማሰናበቱን አስታወቀ።
ክለቡ በፌስቡክ ገፁ የሰፈረው መረጃ ይህን ይመስላል:-
” ቅዱስ ጊዮርጊስን ለሦስት ዓመታት ለማሰልጠን በቅርቡ ፊርማቸውን ያኖሩት ጀርመናዊው አሰልጣኝ ኧርነስት ሚድንድሮፕ በሀገሪቱ ውስጥ ያለው ሁኔታ ስላሳሰበኝና ቤተሰቦቼም በሁኔታው ግራ ስለተጋቡ በሚል ሰበብ ውሌን አፍርሼ እንድሄድ ይፈቀድልኝ ሲሉ ለቦርዱ ጥያቄ አቅርበዋል፡፡ የቅዱስ ጊዮርጊስ የስራ አመራር ቦርድ ምንም እንኳን አሰልጣኙ ያቀረቡት ጉዳይ መሰረተ ቢስና አሳማኝ አለመሆኑን ቢገልጽላቸውም ፈቃደኛ ሆነው ስላልተገኙ ባለው የውል ስምምነት መሰረት አሰልጣኙ የሁለት ወር ደሞዛቸውን ለክለቡ ከፍለው እንዲናበቱ ወስኗል፡፡ ለጊዜው ክለቡን በረዳትነት ያሰለጥኑ የነበሩት ዳቪድስ ማሄር ጊዚያዊ አሰልጣኝ ሆነው እንዲሰሩ ተደርጓል፡፡”
ኧርነስት ሚደንዶርፕ የፈረሰኞቹ ዋና አሰልጣኝ ሆነው የተሾሙት ልክ የዛሬ ወር ነበር።
©ሶከር ኢትዮጵያ