ሰበታ ከተማዎች ከሁለት ቀናት በኃላ በድጋሚ ወደ መደበኛ ልምምድ ተመልሰዋል፡፡
በአሰልጣኝ አብርሀም መብራቱ የሚመሩት ሰበታ ከተማዎች ከደመወዝ ክፍያ እና ከጥቅማ ጥቅም ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ላለፉት ሁለት ቀናት ልምምድ አቁመው የነበሩ ሲሆን ዛሬ ረፋድ ላይ ግን የክለቡ አመራሮች ተጫዋቾቹን የማግባባት ሥራ ከሰሩ በኃላ መደበኛ ልምምዳቸውን በሰበታ ስታዲየም ከውነዋል፡፡ ምንም እንኳን ክለቡ አሁንም ችግሩን መቅረፍ ባይችልም በነገው ዕለት ሙሉ በሙሉ ለመፍታት እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑን ሰምተናል፡፡
ዝግጅት ከጀመረ አጭር ሳምንትን ያስቆጠረው እና ከደመወዝ ጥያቄ ጋር በተገናኘ ለሁለት ቀናት ልምምድ አቋርጦ የተመለሰው ክለቡ የፊታችን ቅዳሜ የኢትዮጵያ ቢትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ሲጀመር ድሬዳዋ ከተማን የሚገጥም ይሆናል፡፡
© ሶከር ኢትዮጵያ