የአሰልጣኞች አስተያየት | ቅዱስ ጊዮርጊስ 0-1 ፋሲል ከነማ

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሁለተኛ ጨዋታ ፋሲል ከነማ ቅዱስ ጊዮርጊስን 1-0 ከረታ በኋላ የቡድኖቹ አሰልጣኞች ለሱፐር ስፖርት ይህንን ብለዋል።

አሰልጣኝ ሥዩም ከበደ – ፋሲል ከነማ

ስለጨዋታው…

“በኮፌዴሬሽን ካፕ ውድድር መሳተፋችን በጣም ጠቅሞናል። በሁሉም ረገድ የተሻለ ሆነን እንድንቀርብም አግዞናል። ቅዱስ ጊዮርጊስን የሚያክል ትልቅ ቡድን ካላሸነፍክ ለሻምፒዮንነት አትጫወትም። ስለዚህ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ዓይነት ቡድኖች የምትወስዳቸው ነጥቦች ናቸው ለሻምፒዮንነት የሚያበቁህ። የሚገባንን አድርገን የምንፈልገውን ነጥብ አግኝተናል። እነርሱም የሚቻላቸውን ለማድረግ ሞክረዋል፤ ግን ሊያሳኩ አልቻሉም።”

ስለ ሱራፌል እና ያሬድ ጉዳት…

“ኳሱን መስርቶ ለማጥቃት በሚደረግ እንቅስቃሴ ውስጥ የያሬድ ሚና የላቀ ነው። የእርሱ መውጣት ክፍተት ቢፈጥረብንም ባለው ነገር ጨዋታውን ተቆጣጥረን ወጥተናል። ጉዳቱ ያን ያህል ከባድ አይደለም። የሱራፌልም ጉዳት በተመሳሳይ ከባድ አይደለም። ለቀጣይ ጨዋታ በሚገባ የምንጠቀምበት ይሆናል።”

አሰልጣኝ ማሂር ዴቪድስ – ቅዱስ ጊዮርጊስ

ስለጨዋታው…

“እንቅስቃሴያችን ጥሩ ነበር። ያገኘናቸውን የጎል ዕድሎች አለመጠቀም ዋጋ አስከፍሎናል። በጨዋታው ውስጥ ብዙ የግብ ዕድሎች መፍጠር ችለናል።”

ስለ ግብጠባቂው ስህተት

“እርሱን በሚያክል ከፍተኛ ልምድ ባለው ትልቅ ግብጠባቂ የማይጠበቅ ስህተት ነው የሰራው”

ስለቀጣይ ጨዋታ ዝግጅት…

“ዛሬ አቅደን የገባነውን ማሳካት አልቻልንም። ሌላ ጨዋታ እንሞክራለን። ስለዚህ በቀጣይ ጨዋታ ራሳችንን አስተካክለን እንቀርባለን።”


© ሶከር ኢትዮጵያ