በጨዋታ ሳምንቱ የመጨረሻ ግጥሚያ ሀዲያ ሆሳዕና ሲዳማ ቡናን 3-1 ካሸነፈ በኋላ የቡድኖቹ አሰልጣኞች ለሶከር ኢትዮጵያ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
አሰልጣኝ ዘርዓይ መሉ – ሲዳማ ቡና
ስለጨዋታው…
“በጨዋታው ተከላካይ ክፍል አካባቢ ተመሳሳይ ስህተቶች ተደግመዋል። በመቀጠል ዛሬ በፌዴሬሽኑ ምክንያት ያልተጠቀምናቸው አራት የውጪ ዜጋ ተጫዋቾች ነበሩን ፤ አራቱም የመጀመሪያ አሰላለፍ ውስጥ ነበሩ። የሥራ እና የመኖሪያ ፍቃድ ሳይጨርሱ አይጫወቱም ተብሎ ዛሬ አራት ሰዓት ላይ ነው ከአሰላለፍ ያወጣናቸው። ዞሮ ዞሮ ተመሳሳይ ስህተቶች ናቸው የተፈጠሩት። በጨዋታው ወደ እንቅስቃሴ ለመመለስ ሞክረናል። በተለይ ከዕረፍት በፊት ያገኘናቸውን ዕድሎች ባለመጠቀማችን እና ተራ ስህተቶችን በመስራታችን ግቦች እንዲቆጠርብን አድርገናል። በእነዚህ ምክንያቶች ልንሸነፍ ችለናል።”
ምክትል አሰልጣኝ ኢያሱ መርሃፅድቅ – ሀዲያ ሆሳዕና
ስለጨዋታው…
“እንደ አጠቃላይ ጨዋታው ቆንጆ የሚባል ነበር ፤ ካለፉት ሁለት ጨዋታዎች ለየት በሚል መልኩ በዛሬው ጨዋታ በመጀመሪያው አጋማሽ ግብ ማስቆጠር መቻላች እና ሦስት ግብ ማስቆጠር ችለናል።”
ስለቡድኑ ደካማ ጎን…
” አሁን ላይ በድክመቶቹ ዙርያ በጥልቀት ማወራት የሚቻልበት ጊዜ አይደለም ፤ ከዚህ በፊት ግብ የማስቆጠር ችግር ነበረብን አሁን ላይ እሱን በተወሰነ መልኩ ቀርፈናል። ነገርግን አሁንም ኳስን ተቆጣጥሮ በመጫወት ረገድ ክፍተቶች አሉብን።”
© ሶከር ኢትዮጵያ