በስድስት ምድቦች ተከፍሎ የሚደረገው የ2013 የኢትዮጵያ አንደኛ ሊግ ሻምፒዮና ውድድር በይፋ ተጀምሯል፡፡
የኢትዮጵያ አንደኛ ሊግ የ2013 የውድድር ዓመት ባለፈው ትናንት ታኅሣሥ 25 በተደረጉ ጨዋታዎች በተመረጡ የተለያዩ ከተሞች በይፋ ተጀምረዋል፡፡ ምድብ 1፣ 2፣ 3፣ 4 እና 6 ላይ ያሉ ክለቦች የመክፈቻ ጨዋታቸውን ያደረጉ ሲሆን በመቐለ የሚደረገው የምድብ አምስት ግን እስከ አሁን የሚጀመርበት ቀን አልያም ውድድሩ ስለመካሄዱ አልታወቀም፡፡
በመጀመሪያው ሳምንት የተደረጉ መርሀ ግብር ውጤቶች እነዚህን ይመስላሉ
ምድብ አንድ (አሰላ)
አምቦ ከተማ 1-1 ሆለታ ከተማ
አሶሳ ከተማ 0-0 ንስር ከተማ
ቡራዩ ከተማ 0-0 ወሊሶ ከተማ
ኤጄሬ ከተማ 3-0 መቱ ከተማ (ፎርፌ)
ምድብ ሁለት (ቢሾፍቱ)
አራዳ ክ/ከተማ 5-1 ሐረር ከተማ
ቢሾፍቱ ከተማ 1-1 መተሐራ ስኳር
ሱሉልታ ከተማ 1-2 ድሬዳዋ ፖሊስ
ሞጆ ከተማ 1-0 ገደብ ሀሳሳ
ምድብ ሦስት (ደብረማርቆስ)
እንጅባራ ከተማ 3-0 ደጋን ከተማ
ጎጃም ደብረማርቆስ 1-1 ዳንግላ ከተማ
ዳሞት ከተማ 2-0 አምባ ጊዮርጊስ
ቆቦ ከተማ 1-1 ደባርቅ ከተማ
አማራ ውሀ ሥራዎች 2-0 መርሳ ከተማ
አራፊ – ደብረማርቆስ
ምድብ አራት (ቡራዩ)
አዲስ ከተማ 2-0 አዲስ አበባ ፖሊስ
ንፋስ ስልክ ክ/ከተማ 2-2 ልደታ ክፍለ ከተማ
ለገጣፎ 01 2-2 መከላከያ ቢ
ሰንዳፋ በኬ 1-1 ጉለሌ ክፍለ ከተማ
ምድብ ስድስት (ሶዶ)
አንጋጫ ከተማ 1-3 ቡሌ ሆራ
ነገሌ ቦረና 0-1 ሀድያ ሌሞ
ጂንካ ከተማ 0-1 ሾኔ ከተማ
ጎፋ ባራንቼ 1-0 ጎባ ከተማ
አረካ ከተማ 1-0 ሮቤ ከተማ
© ሶከር ኢትዮጵያ