ባህር ዳር ከተማ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ – አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎች

የዕለቱ ተጠባቂ ጨዋታ አሰላለፍ እና ወቅታዊ መረጃዎችን እነሆ! 

በአምበልነት እና አሰልጣኝነት የሊጉን ዋንጫ ያነሱበት የቀድሞ ክለባቸውን የሚገጥሙት የባህር ዳር ከተማው አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ ቡድናቸው ሰበታ ከተማን ካሸነፈበት ጨዋታ የሁለት ተጫዋች ለውጥ በማድረግ ጉዳት የገጠመው ሳምሶን ጥላሁንን አሳርፈው አፈወርቅ ኃይሉን፣ በወሰኑ ዓሊ ምትክ ባለፈው ሳምንት ጎል ያስቆጠረው ግርማ ዲሳሳን ተጠቅመዋል። ከጨዋታው በፊት በሰጡት አስተያየትም በፊት መስመሩ ባዬ ገዛኸኝን ዛሬም አለመያዛቸው እንደሚጎዳቸው ሆኖም በስብስቡ ያሉት አጥቂዎች ምርጥ በመሆናቸው ቦታውን እንደሚሸፍኑ እምነታቸውን ገልፀዋል። ለቀድሞ ክለባቸው ያላቸው አክብሮትን የገለፁት አሰልጣኙ አሁን ያሉበት ባህር ዳር ጨዋታውን ያሸንፋል ብለዋል።

አሰልጣኝ ማሒር ዴቪድስ ቅዱስ ጊዮርጊስ ወላይታ ድቻን 1-0 ባሸነፈበት ጨዋታ ከተጠቀሙት የመጀመርያ አሰላለፍ የሁለት ተጫዋቾችን ለውጥ በማድረግ አቤል ያለው እና የአብስራ ተስፋዬን አሳርፈው ማሊያዊው ሮቢን ንጋሌንዴ እና አማካዩ ናትናኤል ዘለቀን በአሰላለፋቸው አካተዋል። ናትናኤል በውድድር ዓመቱ ለመጀመርያ ጊዜ ጨዋታ የሚያደርግ ይሆናል. ደቡብ አፍሪካዊው አሰልጣኝ ጨዋታው ጠንካራ እንደሚሆን ገልፀው የማሸነፍ ሒደታቸውን ለማስቀጠል ወደ ሜዳ እንደሚገቡ ከጨዋታው በፊት ተናግረዋል።

የቡድኖቹ አሰላለፍ ይህንን ይመስላል

ባህር ዳር ከተማ

22 ጽዮን መርዕድ
16 ሳሙኤል ተስፋዬ
15 ሰለሞን ወዴሳ
6 መናፍ ዐወል
13 አህመድ ረሺድ
18 ሳለአምላክ ተገኘ
24 አፈወርቅ ኃይሉ
21 ፍቅረሚካኤል ዓለሙ
14 ፍጹም ዓለሙ
7 ግርማ ዲሳሳ
25 ምንይሉ ወንድሙ

ቅዱስ ጊዮርጊስ

1 ለዓለም ብርሀኑ
14 ሄኖክ አዱኛ
15 አስቻለው ታመነ
24 ኤድዊን ፍሪምፖንግ
3 አማኑኤል ተርፋ
26 ናትናኤል ዘለቀ
5 ሀይደር ሸረፋ
11 ጋዲሳ መብራቴ
27 ሮቢን ንጋላንዴ
28 አማኑኤል ገብረሚካኤል
9 ጌታነህ ከበደ


© ሶከር ኢትዮጵያ