09፡00 ሲል ከሚጀምረው ጨዋታ አስቀድሞ ቀጣዮቹን መረጃዎች እንድትጋሩ ጋብዘናል።
የሜዳው ጥራት ላይ እንደሚመረኮዙ እና ባላቸው ኃይል ማጥቃት ላይ አተኩረው እንደሚገቡ የተናጋሩት አሰልጣኝ ማሂር ዴቪድስ ከሀዲያ ሆሳዕና ጋር ነጥብ ከተጋራው ቡድናቸው ውስጥ ሦስት ለውጦችን አድርገዋል። በለውጦቹም አብዱልከሪም መሀመድ ፣ የአብስራ ተስፋዬ እና አቤል እንዳለ ወደ አሰላለፉ ሲመጡ አማኑኤል ተርፉ ፣ ሀይደር ሸረፋ እና አዲስ ግደይ አርፈዋል።
ጅማ ላይ በሰበታ ተሸንፈው የጨረሱት አሰልጣኝ አስቻለው ኃይለሚካኤል በዛሬው ቡድናቸው ውስጥ በተመሳሳይ የሦስት ተጫዋቾች ለውጥ አድርገዋል። በዚህም ዳንኤል ተሾመ ፣ እዮብ ማቲያስ እና ጀሚል ያዕቆብ ታሪክ ጌትነት ፣ አካሉ አበራ እና በላይ አባይነህን ተክተዋል። አሰልጣኙ የተለየ ዝግጅት ባያደርጉም ደካማ ጎናቸው ላይ መስራታቸውን እና ኳስ ተቆጣጥረው ለመጫወት እንደሚጥሩ ገልፀዋል።
ጨዋታውን በመሀል ዳኝነት እንዲመሩ የተመረጡት አርቢትር ዮናስ ካሳሁን ናቸው።
ሁለቱ ቡድኖች ተከታዮቹን ተጫዋቾች በመጀመሪያ አሰላለፋቸው ውስጥ አካተዋል።
ቅዱስ ጊዮርጊስ
1 ለዓለም ብርሀኑ
14 ሄኖክ አዱኛ
24 ኤድዊን ፍሪምፖንግ
6 ደስታ ደሙ
2 አብዱልከሪም መሀመድ
26 ናትናኤል ዘለቀ
16 የአብስራ ተስፋዬ
18 አቤል እንዳለ
10 አቤል ያለው
28 አማኑኤል ገብረሚካኤል
9 ጌታነህ ከበደ
አዳማ ከተማ
50 ዳንኤል ተሾመ
13 ታፈሰ ሰርካ
20 ደስታ ጊቻሞ
44 ትዕግስቱ አበራ
6 እዮብ ማቲያስ
22 ደሳለኝ ደባሽ
12 ቴዎድሮስ ገብረእግዚአብሄር
5 ጀሚል ያዕቆብ
8 በቃሉ ገነነ
7 ፍሰሀ ቶማስ
10 አብዲሳ ጀማል
© ሶከር ኢትዮጵያ