የአሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያም ቀጣይ ማሪፍያ በቅርቡ ይታወቃል

አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያም የፕሪምየር ሊግ ቡድን ለመያዝ ተቃርበዋል።

ባሳለፍነው የውድድር አጋማሽ ላይ ሀዲያ ሆሳዕናን ተረክበው በኮሮና ቫይረስ ውድድሩ እስከተሰረዘበት ጊዜ ድረስ ቡድኑን እየመሩ መቆየታቸው ይታወቃል። በዚህ ዓመት ክለብ አልባ የነበሩት አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነ ማርያም አሁን ከአንድ ክለብ ጋር ስማቸው በተደጋጋሚ እየተያያዘ ይገኛል።

አሰልጣኝ ፀጋዬን የአሰልጥንልን ጥያቄ ያቀረበላቸው በቅርቡ ከዋና አሰልጣኛቸው ጳውሎስ ጌታቸው ጋር የተለያየው ጅማ አባ ጅፋር እንደሆነ የታወቀ ሲሆን የክለቡ የበላይ ኃላፊዎች ከአሰልጣኙ ጋር ድርድር እያደረጉ መሆኑን ማረጋገጥ ችለናል። በተለያዩ ጉዳዮች ዙርያ ከስምምነት እንደደረሱና ከሰሞኑ የተለየ ነገር ካልተፈጠረ በቀር የአሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነ ማርያም ቀጣይ ማረፊያ ጅማ አባ ጅፋር ሊሆን እንደሚችል ከምንጮቻችን ለማወቅ ችለናል።


© ሶከር ኢትዮጵያ