ለሁለተኛ ዙር የዝውውር እንቅስቃሴውን የጀመረው ወላይታ ድቻ የሽረውን አንበል ለማስፈረም ተስማምቷል።
ከአንተነህ ጉጉሳ እና ደጉ ደበበ ውጪ ልምድ ያለው የመሐል ተከላካይ እጥረት ያለበት ድቻ በተሰረዘው ያለፈው የውድድር ዓመት በስሑል ሽረ ጥሩ ጊዜ ማሳለፍ የቻለው ዮናስ ግርማይ ለማፈረም ከስምምነት ደርሷል። የአንደኛው ዙር ተጠናቆ የዝውውር መስኮቱ ሲከፈት በፌዴሬሽን ውሉ እንደሚፀድቅም ይጠበቃል።
ዮናስ ግርማይ ከዚህ ቀደም ለትራንስ ኢትዮጵያ፣ ሰበታ ከተማ፣ ዳሽን ቢራ፣ መቐለ 70 እንደርታ እና ሱሑል ሽረ መጫወት ችሏል።
ድቻዎች ከየሰናስ በተጨማሪ የግራ መስመር ተከላካዩ አሰረናቀ ሞገስን ወደ ቡድናቸው ለመቀላቀል መስማማታቸው ይታወሳል።
© ሶከር ኢትዮጵያ