የከፍተኛ ሊግ የምድብ ለ የዛሬ ጨዋታዎችም ተሰርዘዋል

የከፍተኛ ሊግ የምድብ ለ የዛሬ ማክሰኞ በኮቪድ 19 የውጤት ማሳወቂያ ማሽን መበላሸት ምክንያት አይከናወኑም፡፡

በሀዋሳ እየተደረገ የሚገኘው የከፍተኛ ሊግ የምድብ ለ ጨዋታዎች ከትላንት ጀምሮ በኮቪድ 19 የተነሳ መርሀግብር የተያዘላቸው ጨዋታዎች እየተካሄዱ አይገኝም፡፡ በትላንትናው ዕለት ሊደረጉ የነበሩ ሦስት መርሀ ግብሮች በኮቪድ 19 የውጤት አለመድረስ ጋር በተገናኘ እንዲሁም ደግሞ የኮቪድ 19 የውጤት ማሳወቂያ ማሽን ብልሽት የገጠመው በመሆኑ ሳይደረግ የቀረ ሲሆን በዛሬው ዕለትም ቤንች ማጂ ቡና ከ ሀምበሪቾ፣ ሻሸመኔ ከተማ ከ ሶዶ ከተማ፣ አቃቂ ቃሊቲ ከ ሀላባ ሊደርጉት የነበረው ጨዋታ በውጤት ማሳወቂያ ማሽኑ እየሰራ ባለመገኘቱ ወደ ሌላ ጊዜ በሚወጣ ፕሮግራም ለመሸጋገር መገደዱን ሶከር ኢትዮጵያ ከአወዳዳሪው አካል አረጋግጣለች፡፡ በአፋጣኝ ይህ ጉዳይ መፈታት ካልቻለም በቀጣዮቹ ቀናት የሚደረጉ የምድቡ ጨዋታዎች በተያዘላቸው ቀን የመደረጋቸው ነገርን አጠራጣሪ አድርጓል፡፡

የከፍተኛ ሊግ የምድብ ለ ጨዋታዎች በሀዋሳ መደረግ ከጀመረ ወራት የሞሉት ሲሆን በተለያዩ ምክንያቶች ውድድሩ መቋረጥ መጀመሩ በበጀት እጥረት ለሚታመሱ ክለቦች ሌላ የራስ ምታትን እንደሚፈጥር ይጠበቃል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ