የሊጉ አክሲዮን ማኅበር የዕግድ ውሳኔ አሳለፈ
በባህር ዳር እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ጨዋታ መነሻነት የጨዋታው ታዛቢው ቅጣት ተጥሎባቸዋል።
የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አክሲዮን ማህበር ዛሬ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ በፃፈው ደብዳቤ ቡድኑ ባህር ዳርን ሲገጥም በታዛቢነት ተመድበው በነበሩት አቶ ፍቃዱ ጥላሁን ላይ የሦስት ወራት ዕገዳ መጣሉን አስታውቋል። ደብዳቤው ላይ እንደተጠቀሰውም የቅጣቱ መንስኤ ታዛቢው የተሟላ ሪፖርት አለማቅረባቸውን በማመናቸው መሆኑ ተጠቁሟል።
ከቅዱስ ጊዮርጊስ የፌስ ቡክ ገፅ ያገኘነው የሊጉ አክሲዮን ማህበር ደብዳቤ ይህንን ይመስላል። ©ሶከር ኢትዮጵያ