4፡00 ሲል የሚጀምረው ጨዋታ ላይ የተደረጉ ለውጦች እና ተጨማሪ መረጃዎችን እነሆ።
የጅማ ቆይታቸው በድል ለማጠናቀቅ መዘጋጀታቸውን የገለፁት አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ ቡድናቸው ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ነጥብ ሲጋራ ከተጠቀሙት አሰላለፍ ውስጥ የሁለት ተጫዋቾች ለውጥ አድርገዋል። በለውጦቹ ወሰኑ ዓሊ እና በረከት ጥጋቡ ወደ አሰላለፍ ሲመጡ አምበሉ ፍቅረሚካኤል ዓለሙ እና ግርማ ዲሳሳ አርፈዋል።
አሰልጣኝ የሱፍ ዓሊ ሽንፈት ቢደራረብብንም የጅማ ቆይታችንን በአሸናፊነት ለማጠናቀቅ ወደ ሜዳ እንገባለን ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። አሰልጣኙ በወላይታ ድቻው ሽንፈት ሲገጥማቸው ከተጠቀሙበት ቀዳሚ ቡድን ውስጥ አራት ማስተካከያዎችን አድርገዋል። ግብ ጠባቂው ጃኮ ፔንዜ በአበበከር ኑሪ ሲለወጥ ሳዲቅ ሴቾ ፣ ሮባ ወርቁ ፣ ውብሸት ዓለማየሁ ደግሞ በቤካም አብደላ ፣ ሙሉቀን ታሪከ እና ብዙአየሁ እንዳሻው ቦታ ተተክተዋል።
ፌደራል ዳኛ ተፈሪ አለባቸው ጨዋታውን በመሀል ዳኝነት ለመምራት የተመደቡት አርቢትር ናቸው።
ቡድኖቹ ይዘውት የሚገቡት የመጀመሪያ አሰላለፍ ይህንን ይመስላል ;-
ባህር ዳር ከተማ
22 ጽዮን መርዕድ
16 ሳሙኤል ተስፋዬ
15 ሰለሞን ወዴሳ
6 መናፍ ዐወል
13 አህመድ ረሺድ
12 በረከት ጥጋቡ
18 ሳለአምላክ ተገኘ
24 አፈወርቅ ኃይሉ
14 ፍጹም ዓለሙ
10 ወሰኑ ዓሊ
25 ምንይሉ ወንድሙ
ጅማ አባ ጅፋር
99 አቡበከር ኑሪ
2 ወንድምአገኝ ማርቆስ
16 መላኩ ወልዴ
23 ውብሸት ዓለማየሁ
14 ኤልያስ አታሮ
21 ንጋቱ ገብረሥላሴ
20 ሀብታሙ ንጉሴ
8 ሱራፌል ዐወል
7 ሳዲቅ ሴቾ
19 ተመስገን ደረሰ
27 ሮባ ወርቁ
©ሶከር ኢትዮጵያ