የአሰልጣኝ ፍስሐ ጥዑመልሳን እና ድሬዳዋ ሊለያዩ ?

በቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ የዘንድሮው የውድድር ዘመን ከሚሰጡት አስተያየት ጋር ተያይዞ መነጋገሪያ ርዕስ የሆኑት አሰልጣኝ ፍስሐ ጥዑመልሳን ከክለቡ ጋር ነገ ይነጋገራሉ።

የቀደሞው የድሬዳዋ ሴቶች ቡድን አሰልጣኝ እና ከ2010 ጀምሮ የወንዶች ቡድን ምክትል አሰልጣኝ በመሆን ሲሰሩ የቆዩት አሰልጣኝ ፍስሐ ጥዑመልሳን ባሳለፍነው የውድድር ዘመን አሰልጣኝ ስምኦን ዓባይን በመተካት ዋና አሰልጣኝ ሆነው እያገለገሉ መሆናቸው ይታወቃል።

አሰልጣኙ በትናንትናው ዕለት ቡድናቸውን ይዘው ወደ ባህር ዳር በመጓዝ ዛሬ የመጀመርያ ልምምዳቸውን እያሠሩ የሚገኙት አሰልጣኙ ከውጤት ማጣት ጋር በተያያዘ የመጀመርያ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው እና በዛሬው ዕለትም ክለቡ አሰልጣኙን ለማናገር ጥሪ አድርጎላቸው ወደ ድሬዳዋ ለመጓዝ ቢያስቡም በረራ ባለመኖሩ የተነሳ ነገ ወደ ድሬዳዋ አምርተው ከክለቡ አመራሮች ጋር እንደሚነጋገሩ ሰምተናል። በምን ጉዳይ ላይ እንደሚነጋገሩ የታወቀ ነገር ባይኖርም ክለቡ እና አሰልጣኙ ተነጋግረው የሚደርሱበትን ጉዳይ ተከታትለን የምናቀርብ ይሆናል።


© ሶከር ኢትዮጵያ