“ፍፁም ቅጣት ምቱ በትክክል ተገቢ ነበር” ፍቃዱ ዓለሙ

ለፍፁም ቅጣት ምቱ መገኘት ምክንያት የሆነው ፍቃዱ ዓለሙ ይናገራል

በባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም የመጀመርያው ዓመት አጋማሽ ተጠናቆ በዛሬው ዕለት ሁለተኛው ዙር ውድድር ሲጀመር የዕለቱ ተጠባቂ ሁለተኛ ጨዋታ በዐፄዎቹ እና በፈረሰኞቹ መካከል ጠንካራ ፉክክር ተደርጎበት በፋሲል ከነማ አንድ ለምንም አሸናፊነት መጠናቀቁ ይታወቃል። ጨዋታው ያለ ጎል ተጠናቀቀ ተብሎ ሲጠበቅ በመጨረሻ ጭማሪ ደቂቃ ላይ ለተሰጠው ፍፁም ቅጣት ምት ተቀይሮ በመግባት ምክንያት የሆነው አጥቂው ፍቃዱ ዓለሙ ስለ ፍፁም ቅጣት ምቱ እና ድሉ ስለ ስለፈጠረበት ስሜት ለሶከር ኢትዮጵያ በዚህ መልኩ አስተያየቱን ሰጥቷል ።

” ተቀይሬ እንደምገባ ሲነገረኝ ፋሲላውያንን ለማስደሰት አንድ ነገር እንደማደርግ አስቤ ነው። ይህም ሆኖ ሦስት ነጥብ ለመገኘቱ ምክንያት በመሆኔ ደስተኛ ነኝ። አስቻለው ወደ ኳሱ ለመሄድ በማደርገው ጥረት አቅጣጫዬን አስቶኛል። ስለዚህ ፍፁም ቅጣት ምቱ በትክክል ተገቢ ነበር። ምክንያቱም ሚዛኔን ስላሳተኝ ማለት ነው። የዛሬው ድል ቡድናችን ወደ ዋንጫ ለሚያደርገው ጉዞ ወሳኝ ነበር። በእኔ ምክንያት ወሳኝ ሦስት ነጥብ በመገኘቱም በጣም ደስተኛ ነኝ። በየትኛውም አጋጣሚ አሰልጠኝ ሥዩም በቀጣይ የሚሰጠኝን ዕድል በመጠቀም ቡድኑ የዋንጫውን ክብር እንዲያሳካ የምችለውን እሰራለሁ።”


© ሶከር ኢትዮጵያ