ከሦስት ቀናት በኋላ በድሬዳዋ እንደሚቀጥል የተነገረው የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ መራዘሙ ተገልጿል።
በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አክሲዮን ማኅበር የበላይነት የሚደረገው የዘንድሮ የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ያለ መቆራረጥ ሲደረግ እንደነበር ይታወሳል። አዲስ አበባ ላይ የጀመረው ሊጉም በጅማ አቆራርጦ ባህር ዳር ላይ እስከ አስራ ስድስተኛ ሳምንት ድረስ ውድድር አከናውኗል። በቀጣይም መጋቢት 26 በድሬዳዋ ይጀምራል የተባለው ሊጉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች እረፍት እንዲያገኙ ለሦስት ቀናት መራዘሙ ተገልጿል።
በዚህም መሠረት መጋቢት 26፣ 27 እና 28 የሚደረጉት ጨዋታዎች ወደ መጋቢት 29፣ 30 እና ሚያዚያ 1 ተሸጋሽገው እንዲደረጉ ውሳኔ ተላልፏል።
© ሶከር ኢትዮጵያ