ፕሪሚየር ሊግ ፡ ደደቢት መሪነቱን ሲቆናጠጥ ድሬዳዋ ከአርባምንጭ አቻ ተለያዩ

በኢትዮጵያ ፕሪሚር ሊግ 13ኛ ሳምንት ዛሬ 2 ጨዋታዎች ተደርገው ደደቢት መሪነቱን የጨበጠበትን ድል ሲያስመዘግብ ድሬዳዋ ከ አርባምንጭ ነጥብ ተጋርተዋል፡፡

መጀመር ከሚገባው እጅግ ዘግይቶ 09፡25 ላይ የተጀመረው የሃዲያ ሆሳዕና እና የደደቢት ፍልሚያ በደደቢት 3-1 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡ የሀዲያ ሆሳዕናው ተከላካይ ውብሸት 5 ቢጫ እያለበት በቋሚ አሰላለፍ ውስጥ በመግባቱ ደደቢት ቅሬታ ያቀረበ ሲሆን ክስም አስመዝግቧል፡፡ ኋላ ላይም ሀዲያ ሆሳዕና ውብሸትን አስወጥቶ ንጋቱ ዱሬን በማስገባት ጨዋታውን ጀምሯል፡፡ ሀዲያ በፌዴሬሽኑ ያልተመዘገቡ የቡድን መሪ ይዞ በመቅረቡም ለጨዋታው መዘግየት ሌላው ተጠቃሽ ምክንያት ሆኗል፡፡

ለደደቢት ዳዊት ፍቃዱ ከርቀት አክርሮ በመምታት የመጀመርያዋን ግብ ሲያስቆጥር ሳሚ ሳኑሚ የሞከረውን ኳስ ጃክሰን ፊጣ ሲመልሰው አየለ ተስፋዬ ተደርቦ በመቆጠሩ 2ኛ ጎል ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ ከእረፍት መልስ በ48ኛው ደቂቃ ዳዊት ፍቃዱ የደደቢትን 3ኛ ግብ ሲያስቆጥር ወደ ቋሚ አሰላለፍ የተመለሰው ዱላ ሙላቱ በ72ኛው ደቂቃ የሀዲያ ሆሳዕናን ግብ አስቆጥሯል፡፡

ድሉ ደደቢትን በ25 ነጥብ የሊጉ መሪ ሲያደርገው ሁለት ጨዋታ የሚቀረው ቅዱስ ጊዮርጊስን በ2 ነጥብ መብለጥ ችሏል፡፡ አሰልጣኝ ግርማ ታደሰን ያገደው ሀዲያ ሆሳዕና ደግሞ የሊጉን ግርጌ በመያዝ የመጀመርያውን ዙር አጠናቋል፡፡

image-37f664ae1f5af6ea6750401d4f45ba7b1f4b784885d351c4aa7610977e95c7e9-V

10፡00 ላይ አርባምንጭ ከተማን ያስተናገደው ድሬዳዋ ከተማ ካለ ግብ አቻ ተለያይቷል፡፡ ጨዋታው እምብዛም ማራኪ ያልነበረ እና የግብ ሙከራ ያልተስተናገደበት ሲሆን ድሬዳዋ በደረጃ ሰንጠረዡ ከፍ ካሉት ቡድኖች ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ማጥበብ ይችል የነበረበትን እድል አምክኗል፡፡ በጨዋታው አርባምንጮች በመከላከል ነጥብ ይዘው የመመለስ እቅዳቸውን አሳክተዋል፡፡

ውጤቱ ሁለቱም ቡድኖች በነበሩበት 5ኛ እና 11ኛ ደረጃ እንዲቆዩ አድርጓቸዋል፡፡

የደረጃ ሰንጠረዥ

jksufhj

የከፍተኛ ግብ አግቢዎች ደረጃ

kbajsghc;l

ቀጣይ የ13ኛ ሳምንት ጨዋታዎች

ማክሰኞ የካቲት 29 ቀን 2008

09፡00 ወላይታ ድቻ ከ ኢትዮጵያ ቡና (ቦዲቲ)

09፡00 መከላከያ ከ አዳማ ከተማ (አአ ስታድየም)

11፡30 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ ኤሌክትሪክ (አአ ስታድየም)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *