በሴካፋ ውድድር የምትሳተፈው ታንዛኒያ በመጨረሻም ባህር ዳር ገብታለች።
ዘጠኝ ሀገራትን የሚያሳትፈው 41ኛው የምስራቅ እና መካከለኛው የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር በደማቅ ሁኔታ በባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም እየተከናወነ ይገኛል። በውድድሩ ከሚሳተፉት ሀገራት መካከል ዛሬ ከሰዓት ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጋር የሚጫወተው የታንዛኒያ ብሔራዊ ቡድን ትናንት ምሽት ባህር ዳር እንደሚገባ ቀድሞ ቢገለፅም ባልታወቀ ምክንያት አዲስ አበባ ላይ አድሮ ጠዋት 2:30 ባህር ዳር ደርሷል።
በተፈሪ መኮንን ሆቴል መቀመጫውን ያደረገው ብሔራዊ ቡድኑ ዛሬ 10 ሰዓት የምድቡ አንደኛ ጨዋታውን ከኮንጎ ጋር ከማድረጉ በፊት ባረፉበት ሆቴል የኮቪድ-19 ምርመራ ማድረጉ ተነግሯል።