ሀዋሳ ከተማ ሁለገቡን ተጫዋች ስድስተኛ ፈራሚ አደድርጎ ወደ ቡድኑ ቀላቅሏል፡፡
በአሰልጣኝ ዘርዓይ ሙሉ እየተመሩ እስከ አሁን አምስት አዳዲስ ተጫዋቾችን አስፈርመው የነበሩት ሀዋሳ ከተማዎች በዛሬው ዕለት ሁለገቡን ተጫዋች መድሀኔ ብርሀኔን በሁለት ዓመት ውል አስፈርመዋል፡፡ የቀድሞው የደደቢት የመስመር አጥቂ፣ የመስመር ተከላካይ እንዲሁም ደግሞ በፊት አጥቂ ስፍራ ላይ ሲጫወት የምናውቀው መድሀኔ በተሰረዘው የ2012 የውድድር ዘመን ወርሀ መጋቢት ወር ስሑል ሽረን ከለቀቀ በኃላ ለአንድ ዓመት ከስድስት ወራት በሀድያ ሆሳዕና አሳልፏል፡፡
ውሉ ከክለቡ ጋር መጠናቀቁን ተከትሎ ከተለያዩ ክለቦች ጋር ስሙ ሲያያዝ የነበረው ተጫዋቹ ማረፊያው በመጨረሻም ሀዋሳ ከተማ ሆኗል።