ከባህር ዳር ከተማ ጋር የተለያየው ግብ ጠባቂ ወደ ወላይታ ድቻ ማምራቱ እርግጥ ሆኗል።
በአርባምንጭ ከተማ የእግርኳስ ህይወቱን የጀመረው ፅዮን እስከ 2011 የውድድር ዓመት ድረስ በዋናው ቡድን ካገለገለ በኋላ ወደ ባህር ዳር ከተማ 2012 ላይ ማምራቱ ይታወሳል። ተጫዋቹ የአንድ ዓመት ውል ከባህር ዳር ጋር ቢቀረውም በስምምነት በመለያየት ከደቂቃዎች በፊት ወደ ወላይታ ድቻ የሚወስደውን ዝውውር አጠናቋል።
መክብብ ደገፉን ወደ ሀዲያ ሆሳዕና የሸኘው ድቻ በቦታው ወንድወሰን አሸናፊን ማምጣቱ አይዘነጋም። አሁን ደግሞ በቦታው ጥሩ ተፎካካሪ እንደሚሆን የሚጠበቀውን ፅዮን ስብስቡን በሁለት ዓመት ውል ተቀላቅሏል።