ሀዋሳ ከተማ ከቀናት በኋላ የቅድመ ውድድር ዝግጅቱን ይጀምራል፡፡
ለቀጣዩ የ2014 የኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ አሰልጣኝ ዘርአይ ሙሉን በሁለት አመት የውል ዕድሜ ወደ ክለቡ ካመጣ በኋላ ጠንካራ ተፎካካሪ ለመሆን የአዳዲስ ተጫዋቾች ዝውውር እንዲሁም የነባሮችን ውል ሲያራዝም ያለፉትን ቀናት ቆይታ ያደረገው ሀዋሳ ከተማ ለፕሪምየር ሊጉ የቅድመ ውድድር ዝግጅት ለማድረግ ለተጫዋቾቹ ጥሪን አድርጓል፡፡
ክለቡ እና አሰልጣኝ ዘርዓይ ሙሉ ለሶከር ኢትዮጵያ እንዳሳወቁት ከሆነ ለሁሉም ተጫዋቾች የቅድመ ምርመራ እና የኮቪድ 19 ህክምና ከተፈፀመላቸው በኋላ የፊታችን ዓርብ ነሐሴ 14 በሀዋሳ ከተማ በይፋ ዝግጅት እንደሚጀምሩ ተገልፆልናል፡፡