አአ ከተማ 2-1 ወራቤ ከተማ
ተጠናቀቀ!!
ጨዋታው በአአ ከተማ 2-1 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡ ሁለተኛው አጋማሽ ቀዝቃዛ እንቅስቃሴ ቢታይበትም በርካታ ፋውሎች ተስተናግደውበታል፡፡
84′ ጎልልል አአ ከተማ
አቤል ዘውዱ ከመስመር የተሻገረለትን ኳስ ተጠቅሞ አአ ከተማን በድጋሚ መሪ አድርጓል፡፡
75′ ቀይ ካርድ
የወራቤው ፈድሉ ሀምዛ በ2ኛ ቢጫ ካርድ ከሜዳ ተወግዷል፡፡
65′ ሁለቱም ቡድኖች ከመጀመርያው አጋማሽ እጅግ የወረደ እንቅስቃሴ እያሳዩ ይገኛሉ፡፡
ተጀመረ
ሁለተኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለጊዜ ተጀምሯል፡፡
—-
እረፍት
የመጀመርያው አጋማሽ በአቻ ውጤት ተጠናቋል፡፡
45+1′ ጎልልል!!! ወራቤ ከተማ
አብዱራዛቅ የግል ጥረቱን ተጠቅሞ ለወራቤ የቻነት ግብ አስቀቆጥሯል፡፡
36′ ጎልልል!!! አአ ከተማ
ምንያምር ጴጥሮስ የግብ ጠባቂውን ትኩረት ማነስ ተመልክቶ የመታው ኳስ የአዲስ አበባ ቀዳሚ ጎል ሆናል፡፡
30′ ሙሃጅር መኪ ከርቀት አክርሮ የመታውን ኳስ የወራቤው ግብ ጠባቂ ተመስገን አውጥቶበታል፡፡
24′ ከማዕዘን ምት የተሻገረውን ኳስ ዘሪሁን ሞክሮ ግብ ጠባቂውን ቢያልፍም የወራቤ ተከላካዮች ተረባርበው አውጥተውታል፡፡
19′ ለአአ ከተማ ቢንያም አማረ የሞከረውን ኳስ ግብ ጠባቂው ተመስገን አውጥቶበታል፡፡
1′ ተጀመረ
በአአ ከተማ እና ወራቤ ከተማ መካከል የሚደረገው ጨዋታ ተጀምሯል፡፡
የአአ ከተማ አሰላለፍ
ተክለማርያም ሻንቆ – ሙሃጅር መኪ – ቢንያም አማረ – ሰይፈ መገርሳ – ሚልዮን ብሬ – ዘሪሁን ብርሃኑ – ዳዊት ማሞ – ዮናታን ብርሃነ – ምንያምር ጴጥሮስ – ሀይሌ እሸቱ – ሃይለየሱስ መልካ
የወራቤ ከተማ አሰላለፍ
ተመስገን ጮኖሬ – ገረሱ ሸመና – ክብረት ታደሰ – አብዱራዛቅ ናስር – ሚኪያስ አለማየሁ – ዘነበ ቴንታ – ካሳ ከተማ – መሃመድ ከድር – ሮባ ዱከም – ሙስጣፋ ያሲን – ፈድሉ ሀምዛ
– – – – – –
ፌዴራል ፖሊስ 0-1 ጅማ አባ ቡና
ተጠናቀቀ !!!
ጨዋታው በጅማ አባ ቡና አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡
69′ ለጅማ አባ ቡና ተቀይሮ የገባው አዲሱ የሞከረው ኳስ አግዳሚውን ገጭቶበታል፡፡
67′ ከግቡ መቆጠር በኀላ ጅማ አባ ቡናዎች ተጨማሪ ግብ ለማስቆጠር ጫና በመፍጠር ላይ ይገኛል፡፡
60′ ጎልልል ጅማ አባ ቡና
ከመስመር የተሻገረውን ኳስ የፌዴራል ፖሊስ ተከላካዮች በአግባቡ ማራቅ ባለመቻላቸው ኦሜ መሃመድ አግኝቶት አሰቆጥሯል፡፡
52′ ከጅማ አባ ቡና በኩል ተቀይሮ የገባው ሳሙኤል ብርሃኑ የሞከረው ኳስ የግቡ አግዳሚ ገጭቶበታል፡፡
46′ ነፃነት ለገሰ ከቅጣት ምት የሞከረው ኳስ ለጥቂት ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡ ይህ የፌዴራል ፖሊስ የመጀመርያ ሙከራ ነው፡፡
ተጀመረ
2ኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጀምሯል፡፡
– – – –
ተጠናቀቀ!
የመጀመርያው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ካለግብ ተጠናቋል፡፡ ፌዴራል ፖሊስ ሙሉ ለሙሉ በመከላከል ፣ ጅማ አባ ቡናዎች ደግሞ ኳስ ተቆጣጥሮ ጫና በመፍጠር ተንቀሳቅሰዋል፡፡
35′ ሱራፌል አወል ያመቻቸለትን ኳስ ኦሜ መሃመድ ሳይጠቀምበት ቀርቷል፡፡
22′ ኦሜ መሃመድ ከግብ ጠባቂው ጋር አንድ ለአንድ ተገናኝቶ የሞከረው ለጥቂት ወጥቶበታል፡፡
15′ ጅማ አባ ቡና ኳስ ተቆጣጥሮ በመጫወት እና ወደ ግብ በመድረስ የተሸለ እቅስቃሴ እያደረጉ ይገኛሉ፡፡ ነገር ግን ኢላማውን የጠበቀ ሙከራ ማድረግ አልቻሉም፡፡
1′ ጨዋታው ተጀምሯል፡፡
07:45 የፌዴራል ፖሊስ እና ጅማ አባቡና ተጫዋቾች ሰውነታቸውን ለማፍታታት ወደ ሜዳ ገብተዋል፡፡
የፌዴራል ፖሊስ አሰላለፍ
ኤጁሉ ኢላሌ – ክብሮም እሸቱ – ብርሃኑ ገብረስላሴ – በድሉ ሰለሞን – አስቻለው አየለ – ሀለፎም ካህሳይ – ማንደፍሮ አክሊሉ – ኄኖክ አሰፋ – አቤል ፋንታሁን – ፓም ጀምስ – መብራህቱ ወልዴ
የጅማ አባ ቡና አሰላለፍ
ዘላለም ልኬሳ – ተመስገን ደረሰ – ጀማል ያዕቆብ – ከድር ሙስጣፋ – ዳንኤል ስለሺ – ዳዊት ተፈራ – ቢንያም ሀይሌ – ኪዳኔ አሰፋ – በኃይሉ በለጠ – ኦሜ መሃመድ – ሱራፌል አወል
– – – – – –
በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ምድብ ለ 10ኛ ሳምንት ዛሬ ሁለት ከፍተኛ ግምት የሚሰጣቸው ጨዋታዎች አበበ ቢቂላ ይደረጋሉ፡፡ በ08፡00 የምድቡ መሪ ጅማ አባ ቡና ከ ፌዴራል ፖሊስ ሲጫወቱ 10:00 ላይ ሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው አዲስ አበባ ከተማ ወራቤ ከተማን ያስተናግደል፡፡ እነዚህን ሁለት ጨዋታዎች በቀጥታ የጽሁፍ ስርጭት በዚሁ ገጽ ላይ እናደርሳችኋላን፡፡
መልካም ውሎ!