አዲስ አበባ ከተማ ወደ ሊጉ ማደጉን ተከትሎ ቃል የተገባለትን ሽልማት በነገው ዕለት ይረከባል።
የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ምድብ ለ’ን በበላይነት በማጠናቀቅ የሀገሪቱን ከፍተኛ የሊግ እርከን የተቀላቀለው አዲስ አበባ ከተማ በመዲናው መስተዳደር ሽልማት እንደሚበረከትለት ቃል ተገብቶ ነበር። መስተዳደሩም ዘግየት ብሎም ቢሆን ቃል የገባውን የማበረታቻ ሽልማት በነገው ዕለት እንደሚያበረክት ታውቋል።
በሀዋሳ እና ወልዲያ በነበረው የከፍተኛ ሊግ ውድድር ክለቡን ያገለገሉ ተጫዋቾች፣ አሠልጣኞች እና ባለድርሻ አካላትም ነገ ከ12 ሰዓት ጀምሮ በሀያት ሪጀንሲ ሆቴል በሚዘጋጀው የእውቅና አሠጣጥ መርሐ-ግብር ላይ ሽልማት እንደሚበረከትላቸው አውቀናል።