የ2015 የካፍ ኦሬንጅ ቻምፒዮንስ ሊግ አሸናፊ የሆነው የዲሞክራቲክ ሪፑብሊክ ኦፍ ኮንጎው ቲፒ ማዜምቤ ክብሩን የማስጠበቅ ዘመቻውን ነገ በባህርዳር ስታድየም የኢትዮጵያ ቻምፒዮኑ ቅዱስ ጊዮርጊስን በመግጠም ይጀምራል፡፡
ጥቁር እና ነጭ ለባሾቹ አርብ እለት 19 ተጫዋቾች ፣ የቡድን መሪ ፣ 3 ጋዜጠኞች እንዲሁም 6 የአሰልጣኞች ቡድን አባላትን በመያዝ በአዲስ አበባ በኩል አድርገው ወደ ባህርዳር በማምራት ግራንድ ሆቴል ያረፉ ሲሆን ከነገው ጨዋታ በፊት የመጨረሻ ልምምዳቸውን 10፡00 ላይ ጨዋታውን በሚያደርጉበት ግዙፉ የባህርዳር ስታድየም አድርገዋል፡፡
በልምምድ ፕሮግራሙ ላይ ከሉሙምባሺ የመጡት 19 ተጫዋቾች በሙሉ ልምምድ ያደረጉ ሲሆን ረጃጅም ኳሶች ፣ የተሻጋሪ ኳሶች አጠቃቀም ፣ የፍፁም ቅጣት ምት አጠቃቀም እና የአካል ብቃት ልምምዶችን ሰርተዋል፡፡ ለሁለት በመከፈልም ተጫውተዋል፡፡
ቅዱስ ጊዮርጊስን የሚገጥመው የቲፒ ማዜምቤ ቡድን ይህንን ይመስላል፡-
ግብ ጠባቂዎች
ኤይሜ ባኩላ ፣ ሮበርት ኪያዳባ ፣ ሲልቪያን ግቦሁዎ
ተከላካዮች
ዮኤል ኪምዋኪ ፣ ካባሶ ቾንጎ ፣ ኪሊትሾ ካሱሱላ ፣ ያው ፍሪምፖንግ ፣ ሳሊፍ ኩሊባሊ ፣ ሊዩንዳማ
አማካዮች
ቦካዲ ቦፔ ፣ ኮፊ ኮዋሜ ፣ አድጄይ ፣ ናታን ሲንካላ ፣ ጊቭን ሲንጉሉማ ፣ ሜሻክ ኤልያ
አጥቂዎች
ሶሎሞን አሳንቴ ፣ ቶማስ ኡሊሙዌንጉ ፣ ጆናታን ቦሊንጊ ፣ አዳማ ትራኦሬ