የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ የምድብ ድልድል ይፋ ሆኗል

በሁለትም ምድብ ተከፍሎ የሚካሄደው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ የምድብ ድልድል በቤስት ዌስተርን ሆቴል ይፋ ሆኗል።

አስራ አምስተኛ የውድድር ዓመቱን ያስቆጠረው የመዲናዋ ትልቁ ውድድር የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ስምንት ክለቦችን በማሳተፍ ከመስከረም 15-30 ድረስ የሚከናወን ይሆናል። በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግስ አገልግሎት ሰጪ አስተባባሪ ዣንጥረር አባይ የስፖርት ኮሚሽን ከሚሽነር አቶ በላይ ደጀን የአዲስ አበባ እግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝደንት ጋሽ አስራት ኃይሌ እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመውበታል።

በቤስት ዌስተርን ሆቴል በተከናወነው የምድብ ድልድል ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ኢትዮጵያ ቡና በውድድሩ ላይ ካላቸው ከፍተኛ ተሳትፎ አንፃር በአንድ ምድባ እንዳይሆኑ በማድረግ የምድብ አባት እንዲሆኑ ተደርጎ የዕጣ ማውጣቱ ሥነ ስርዓት ተከናውኗል።

በዚህም መሠረት

ምድብ ሀ

ኢትዮጵያ ቡና
አዲስ አበባ ከተማ
መከላከያ
ሙኑኪ ኤፍ ሲ(ደቡብ ሱዳን)

ምድብ ለ

ቅዱስ ጊዮርጊስ
ባህር ዳር ከተማ
አደማ ከተማ
ፋሲል ከነማ

አጠቃላይ በዕጣ ማውጣት ሥነ ስርዓቱ ላይ የተበሱ ነጥቦችን ከቆይታ በኃላ ይዘን የምንመለስ መሆኑን ከወዲሁ እንገልፃለን