የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የምድብ ለ 10ኛ ሳምንት ዛሬ አበበ ቢቂላ ላይ በተደረጉ ጨዋታዎች ሲጀምሩ የምድቡ መሪዎች ከተከታዮቻቸው ያላቸውን ርቀት የሚያሰፉበት ድል ማስመዝገብ ችለዋል፡፡
8፡00 ላይ ፌዴራል ፖሊስን የገጠመው ጅማ አባ ቡና 1-0 በማሸነፍ መሪነቱን አስጠብቋል፡፡ የጅማ አባ ቡናን የድል ግብ በሁለተኛው አጋማሽ ከመረብ ያሳረፈው አጥቂው ኦሜ መሃመድ ነው፡፡ ከ32 የከፍተኛ ሊግ ክለቦች እስካሁን ሽንፈት ያላስተናገደው ብቸኛ ክለብ ጅማ አባ ቡና ነጥቡን 26 በማድረስ መሪነቱን እንደያዘ ወደ 11ኛው ሳምንት ተሻግሯል፡፡
10፡00 ላይ 4ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ወራቤ ከተማን ያስተናገደው አዲስ አበባ ከተማ በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች ባገኛት የማሸነፍያ ግብ ታግዞ 3 ነጥብ ይዞ ወጥቷል፡፡ አዲስ አበባ ከተማዎች በ36ኛው ደቂቃ ምንያምር ጴጥሮስ ባስቆጠረው ግብ ሲመሩ ወራቤ ከተማዎች በአብዱራዛቅ ናስር ግብ የመጀመርያውን አጋማሽ በአቻ ውጤት አጠናቀዋል፡፡ በ2ኛው አጋማሽ 85ኛው ደቂቃ ላይ አቤል ዘውዱ የአዲስ አበባ ከተማን የማሸነፍያ ግብ አስቆጥሮ ጨዋታው በአዲስ አበባ ከተማ 2-0 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡ ድሉ አዲስ አበባ ከተማ በ25 ነጥቦች 2ኛ ደረጃውን እንዲያስጠብቅ ሲያደርገው ተሸናፊው ወራቤ ከተማ ደረጃውን የማሻሻል እድሉን አበላሽቶበታል፡፡
የምድብ ለ የደረጃ ሰንጠረዥ ይህንን ይመስላል፡-
የከፍተኛ ሊጉ 10ኛ ሳምንት ቀሪ 14 ጨዋታዎች ነገ ይደረጋሉ፡፡
ምድብ ሀ
07፡00 – ኢትዮጵያ ውሃ ስፖርት ከ አማራ ውሃ ስራ (አበበ ቢቂላ)
09፡00 – መቐለ ከተማ ከ ባህርዳር ከተማ (መቐለ)
09፡00 – ሰሜንሸዋ ደብረብርሃን ከ አክሱም ከተማ (ደብረብርሃን)
09፡00 – ወሎ ኮምቦልቻ ከ ወልድያ (ኮምቦልቻ)
09፡00 – ሙገር ሲሚንቶ ከ ወልዋሎ (መድን ሜዳ)
09፡00 – ሱሉልታ ከተማ ከ ኢትዮጵያ መድን (ሱሉልታ)
09፡00 – አአ ፖሊስ ከ ሰበታ ከተማ (አበበ ቢቂላ)
09፡00 – ፋሲል ከተማ ከ ቡራዩ ከተማ (ጎንደር)
ምድብ ለ
09፡00 – ሻሸመኔ ከተማ ከ ጅማ ከተማ (ሻሸመኔ)
09፡00 – ደቡብ ፖሊስ ከ ድሬዳዋ ፖሊስ (ሀዋሳ)
09፡00 – ነቀምት ከተማ ከ አርሲ ነገሌ (ነቀምት)
09፡00 – ጂንካ ከተማ ከ አአ ዩኒቨርሲቲ (ጂንካ)
09፡00 – ባቱ ከተማ ከ ነገሌ ቦረና (ባቱ)
09፡00 – ናሽናል ሴሜንት ከ ሀላባ ከተማ (ድሬዳዋ)