መስከረም 26 እና 30 ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጋር የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ የሚያደርገው የደቡብ አፍሪካ ብሔራዊ ቡድን ከደቂቃዎች በፊት ለተጫዋቾች ጥሪ አስተላልፏል።
ኳታር ለምታስተናግደው የዓለም ዋንጫ ለማለፍ በየአህጉራቱ የሚገኙ ብሔራዊ ቡድኖች የማጣሪያ ጨዋታዎችን እያደረጉ እንደሆነ ይታወቃል። በአህጉራችን አፍሪካም ብሔራዊ ቡድኖች በምድብ ተከፋፍለው የማጣሪያ ጨዋታቸውን እያደረጉ ይገኛሉ። በዚሁ የማጣሪያ ጨዋታዎች በምድብ ሰባት ከጋና፣ ደቡብ አፍሪካ እና ዚምባቡዌ ጋር የተደለደለው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድንም ሁለት ጨዋታዎችን አድርጎ ሦስት ነጥብ መያዙ ይታወቃል። በቀጣይ ደግሞ ብሔራዊ ቡድኑ መስከረም 26 በሜዳው ከአራት ቀናት በኋላ መስከረም 30 ደግሞ ከሜዳው ውጪ የደቡብ አፍሪካ አቻውን የሚገጥም ይሆናል።
ለእነዚሁ ሁለት ወሳኝ ጨዋታዎች አሠልጣኝ ውበቱ አባተ በትናንትናው ዕለት ለ25 ተጫዋቾች ጥሪ ያደረጉ ሲሆን ተጋጣሚያቸው ደቡብ አፍሪካም ከደቂቃዎች በፊት ለተጫዋቾች ጥሪ አስተላልፏል። በዚህም አሠልጣኝ ሁጎ ብሮስ ለ34 ተጫዋቾች ጥሪ ማስተላለፋቸውን የሀገሪቱ ብዙሃን መገናኛዎች እየዘገቡ ይገኛሉ። የምድቡ መሪ የሆኑት ደቡብ አፍሪካዎች ምንም እንኳን አሁን ላይ ለ34 ተጫዋቾች ጥሪ ቢያስተላልፉም በባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም እና በኤፍ ኤን ቢ ስታዲየም ለሚደረጉት ወሳኝ ፍልሚያዎች የሚጠቀሟቸውን 23 ተጫዋቾች ከአራት ቀናት በኋላ እንደሚለዩ ተጠቁሟል።
ጥሪ የቀረበላቸው 34 ተጫዋቾች የሚከተሉት ናቸው 👇