የውድድር ዓመቱን መክፈቻ ጨዋታ የተመለከቱ ነጥቦችን እንዲህ አንስተናል።
የ2014 ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የሁለት ጊዜ አሸናፊው ሀዋሳ ከተማን ከአንድ ጊዜ ባለ ድሉ ጅማ አባ ጅፋር ጋር በማገናኘት ይጀምራል። የአሰልጣኝ ለውጥ በማድረግ ዓመቱን የሚጀምሩት ሁለቱ ቡድኖች በመክፈቻ ጨዋታ ሲገናኙ ከ2010 በኋላ ለሁለተኛ ጊዜ ይሆናል።
በስብስቡ ውስጥ ዐምና የነበሩ በርከት ያሉ ተጫዋቾችን አሁንም የያዘው ሀዋሳ ከተማ ደጋፊዎች መግባት በሚጀምሩበት ዓመት ቀዳሚውን ጨዋታ በከተማው የማድረግ ዕድልን አግኝቷል። ይህም ቡድኑ በተሻለ የማሸነፍ ፍላጎት ማጥቃትን ያማከለ የጨዋታ ዕቅድ ወደ ሜዳ ይዞ እንዲገባ ያደርገዋል። በሌላ በኩል ተጋጣሚው ጅማ አባ ጅፋር እንደ አዲስ ያዋቀረውን ቡድን ይዞ ጨዋታውን ሲጀምር ጥንቃቄ አዘል አቀራረብን እንደሚያስመለክተን ይጠበቃል።
የተጋጣሚዎቹ ስብስብ የዝግጅት ጊዜውን ጨርሶ ለነገው ጨዋታ ሲደርስ ያለምንም የጉዳት ዜና ነው።
ጨዋታውን በመሀል ዳኝነት የሚመሩት ኢንተርናሽናል ዳኛ ኃይለየሱስ ባዘዘው ይሆናሉ።
ሁለቱ ቡድኖች በሊጉ ስድስት ጊዜ ተገናኝተው ተመጣጣኝ ውጤት አሰዝግበዋል። ሁለቱን ሀዋሳ ሲያሸንፍ አንዱን ጅማ አሸንፎ የአምናዎቹን ጨምሮ በሦስት ጨዋታዎች ነጥብ ተጋርተዋል። ሀዋሳ 7 ፣ ጅማ 6 ጎሎችን አስቆጥረዋል። ከዚህ ቀደም ሁለቱ ቡድኖች በሊግ መክፈቻ ተገናኝተው የሚያውቁ ሲሆን በ2010 ጅማ ላይ ተጫውተው ጅማ አባጅፋር በኦኪኪ አፎላቢ ሁለት ጎሎች 2-0 አሸነፍፏል።
የሁለቱን ክለቦች የክረምት ወቅት ዝግጅት እና በቀጣይ የሚኖራቸውን መልክ በሰፊው ያወሳንባቸውን ፅሁፎች ከዚህ በታች ያገኛሉ።
ሀዋሳ ከተማ
https://soccerethiopia.net/football/7150711
ጅማ አባ ጅፋር
https://soccerethiopia.net/football/7165811