የሳምንቱን ስድስተኛ ጨዋታ በዳሰሳችን እንዲህ ቃኝተነዋል።
አምና ከግማሽ በኋላ በሾማቸው አሰልጣኝ ገብረመድህ ኃይሌ ስር የሚገኘው ሲዳማ ቡና በስብስቡ ላይ በርከት ያሉ ለውጦች ሲያደርግ በነገው ጨዋታ ጥንቃቄ አዘል የሆነ እና መስመሮችን በመጠቀም በቶሎ ጎል ላይ ለመድረስ የመሞከር መልክ እንደሚኖረው ይጠበቃል። ከአሰልጣኝ ካስዬ አራጌ ጋር የሚቀጥለው ኢትዮጵያ ቡና በአጨዋወቱ ላይ ለውጥ እንደማይኖር ሲጠበቅ ከግብ ጠባቂው ጀምሮ ኳስ መስርቶ የማጥቃት ዕቅዱ ሜዳ ላይ እንደሚታይ ይገመታል።
ጨዋታው አምና በኮከብ ግብ አግቢነት ላጠናቀቀው አቡበከር ናስር የተለየ ይመስላል። ኮከብ ከሆነባቸው 29 ጎሎች በሁለት ሐት-ትሪክ ስድስቱን ሲዳማ ቡና ላይ ማስቆጠሩ ነገ የትኩረት ማዕከል እንዲሆን ያደርገዋል።
ሲዳማ ቡና በስብስቡ ላይ የጉዳትም ሆነ የቅጣት ዜና የለበትም። በኢትዮጵያ ቡና በኩል በአፍሪካ ኮንዴፌሬሽን ዋንጫ ከዩ ኡር ኤ ጋር የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ ሲያደርግ ጉዳት የገጠመው ሚኪያስ መኮንን ባለማገገሙ የነገው ጨዋታ ያልፈዋል።
ተመጣጣኝ በሆነው የሊግ ግንኙነት ታሪካቸው ለ22 ጊዜ ሲገናኙ ሲዳማ ቡና 8 ኢትዮጵያ ቡና ደግሞ 7 ጊዜ አሸንፈፈው ቀሪ 7 ጨዋታዎችን አቻ ተለያይተዋል። በጨዋታዎቹ ሲዳማ ቡና 27 ፣ ኢትዮጵያ ቡና ደግሞ 30 ጎሎችን አስቆጥረዋል።
ፌደራል ዳኛ አሸብር ሰቦቃ ጨዋታውን በመሀል ዳኝነት እንደሚመሩት ታውቋል።
የሁለቱን ክለቦች የክረምት ወቅት ዝግጅት እና በቀጣይ የሚኖራቸውን መልክ በሰፊው ያወሳንባቸውን ፅሁፎች ከዚህ በታች ያገኛሉ።
ሲዳማ ቡና
https://soccerethiopia.net/football/7159211
ኢትዮጵያ ቡና
https://soccerethiopia.net/football/7175711