የሉሲዎቹ አሰላለፍ ታውቋል

ከሰዓታት በኋላ ከዩጋንዳ አቻው ጋር የሚጫወተው የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን አሠልላፍ ይፋ ሆኗል።

በሞሮኮ አስተናጋጅነት ለሚከናወነው የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ የማጣሪያ ጨዋታዎችን ማድረግ የጀመረው የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከሦስት ቀናት በፊት የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ለማድረግ ወደ ዩጋንዳ ካምፓላ አምርቷል። ጨዋታው ዛሬ ከቀኑ 10 ሰዓት በሴንት ሜሪ ስታዲየም ሲደረግ አሠልጣኝ ብርሃኑ ግዛውም የሚጠቀሙት የመጀመሪያ አስተላለፍ ታውቋል።  

ግብ ጠባቂ

22 ታሪኳ በርገና

ተከላካይ

13 ናርዶስ ጌትነት

21 ሀሳቤ ሙሶ

4 መስከረም ካንኮ

16 እፀገነት ብዙነህ

አማካዮች

6 እመቤት አዲሱ

14 ህይወት ደንጌሶ

12 አረጋሽ ካልሳ

አጥቂዎች

17 ሴናፍ ዋቁማ

10 ሎዛ አበራ(C)

8 መዲና አወል