13ኛው የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ የሚደረግበት ቀን እና ቦታ ታውቋል።
የኢትዮጵያ እግርኳስ የበላይ አካል የሆነው የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በየዓመቱ ጠቅላላ ጉባኤውን በተመረጠ ስፍራ እንደሚያከናውን ይታወቃል። የአሁኑ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ደግሞ ህዳር 25 እና 26 እንደሚከናወን የፌዴሬሽኑ የጽሕፈት ቤት ሀላፊ አቶ ባህሩ ጥላሁን በማህበራዊ ገፃቸው ይፋ አድርገዋል። ዋና ፀሃፊው አያይዘው ጠቅላላ ጉባኤው በአርባምንጭ ከተማ እንደሚደረግ አመላክተዋል።
ፌዴሬሽኑ በጉባኤው የሚቀርቡ አጀንዳዎችን በቀጣይ ይፋ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።