በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ከቀናት በኋላ ከቦትስዋና ጋር ጨዋታ የሚጠብቀው የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች የሴቶች ብሔራዊ ቡድን ለተጫዋቾች ጥሪ አስተላልፏል።
በኮስታሪካ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የዓለም ከ20 ዓመት በታች የሴቶች ዋንጫ ውድድር ላይ ለመካፈል የማጣሪያ ጨዋታዎችን እያደረገ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በምስራቅ እና መካከለኛው የአፍሪካ ዋንጫ ካሳካው ድል ማግስት ለቀጣይ የማጣሪያ ዙር በነገው ዕለት ተጫዋቾች እንደሚሰባሰቡ ቀድመን ዘግበን ነበር። የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ከደቂቃዎች በፊት ባወጣው መረጃ ደግሞ አሠልጣኝ ፍሬው እና ረዳቶቹ ለ22 ተጫዋቾች ጥሪ ማቅረባቸውን ያትታል።
ጥሪ የቀረበላቸው ተጫዋቾች የሚከተሉት ናቸው።
ግብ ጠባቂዎች
ባንቺአየው ደመላሽ (ባህር ዳር)፣ እየሩሳሌም ሎራቶ (አዳማ)፣ ገነት ኃይሉ (ኤሌክትሪክ)
ተከላካዮች
ብርቄ አማረ (ድሬዳዋ)፣ ናርዶስ ጌትነት (አዳማ)፣ ነጻነት ጸጋዬ (መከላከያ)፣ ቤተልሄም በቀለ (መከላከያ)፣ ዓይናለም አደራ (መከላከያ)፣ መስከረም ኢሳይያስ (ኤሌክትሪክ)፣ ብዙዓየሁ ታደሰ (ንግድ ባንክ)፣
አማካዮች
ማዓድን ሳሕሉ (መከላከያ)፣ ገነት ኃይሉ ሀይዴቦ (መከላከያ)፣ እጸገነት ግርማ (መከላከያ)፣ መሳይ ተመስገን (መከላከያ)፣ ኚቦኝ የን (ኤሌክትሪክ)፣ አረጋሽ ካልሳ (ንግድ ባንክ)
አጥቂዎች
ቤተልሄም ታምሩ (ድሬዳዋ)፣ ቱሪስት ለማ (ሀዋሳ ከተማ)፣ ረድኤት አስረሳኸኝ (ሀዋሳ ከተማ)፣ ዮርዳኖስ ምዑዝ (ንግድ ባንክ)፣ አርያት ኦዶንግ (አዲስ አበባ)፣ ንግስት አስረስ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)
ከላይ የተዘረዘሩት 22 ተጫዋቾች ነገ 7 ሰዓት በካፍ የልዕቀት ማዕከል ሪፖርት እንዲያደርጉ የተጠቆመ ሲሆን መደበኛ ልምምድም በማግስቱ ሀሙስ እንደሚጀምር ተሰምቷል።