ጥቅምት 7 የጀመረው የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ከብሔራዊ ቡድን እረፍት በኋላ ከነገ በስትያ የአራተኛ ሳምንት ጨዋታዎችን በማድረግ እንደሚቀጥል ይታወቃል። የሊጉ የበላይ አካል ከውድድሩ የሥርጭት መብት ባለቤት ዲ ኤስ ቲቪ ጋር በመሆን ከዚህ ቀደም ባወጡት መርሐ-ግብሮች ላይ የቅዳሜ እና እሁድ ጨዋታዎች 8 እና 12 ሰዓት ላይ ይደረጉ ነበር። አሁን በተገኘ መረጃ ደግሞ ሁለቱ አካላት ባደረጉት ንግግር የቅዳሜ እና እሁድ የመጀመሪያ ጨዋታዎች ሰዓት በወጥነት 9 ሰዓት እንደሚጀምሩ ታውቋል።
ይህ ቢሆንም ግን በአዘቦት ቀን የሚደረጉ ጨዋታዎች ምንም የሰዓት ሽግሽግ እንዳልተደረገባቸው አውቀናል። ይህንን ተከትሎ ከአራተኛ ሳምንት እስከ 9 ሳምንት በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ስታዲየም የሚደረጉ ሁሉም ጨዋታዎች 9 እና 12 ሰዓት ላይ የሚደረጉ ይሆናል።