የአራተኛ ሳምንት የሦስተኛ ቀን የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ የመጀመሪያ ጨዋታን የተመለከቱ አሁናዊ መረጃዎች ይዘን ቀርበናል።
ሁለት ተከታታይ ድሎችን ያስመዘገቡት ወላይታ ድቻዎች በሦስተኛ ሳምንት የሊጉ መርሐ-ግብር አዳማ ከተማን ካሸነፉበት ጨዋታ አንድ ለውጥ ብቻ አድርገዋል። በዚህም በቤተሰብ ሀዘን ምክንያት በአሁኑ ሰዓት ስብስብ ውስጥ የሌለው አንተነህ ጉግሳን በቃልኪዳን ዘላለም ተክተዋል።
እስካሁን በሊጉ ሦስት ነጥብ ካላገኙ አራት ክለቦች መካከል አንዱ የሆነው ኢትዮጵያ ቡና ከድል ጋር ለመታረቅ ከሰበታ ከተማ ጋር ያለ ምንም ግብ አቻ ከተለያየበት ጨዋታ አራት ለውጥ አድርገዋል። በለውጦቹም ኃይሌ ገብረትንሳይ፣ ቴዎድሮስ በቀለ፣ ሮቤል ተክለሚካኤል እና አቤል እንዳለን አርፈው ሥዩም ተስፋዬ፣ ዊልያም ሰለሞን፣ ወንድሜነህ ደረጄ እና አላዛር ሺመልስ ወደ ሜዳ ገብተዋል።
አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማሪያም የዕረፍት ጊዜው ለዝግጅት እንዳገዛቸው በመናገር ጨዋታው ተጠባቂ መሆኑን ገልፀዋል። ተጋጣሚታቸው ኳስ ይዞ የሚጫወት መሆኑ እና ጥሩ ስብስብ ያለው በመሆኑ በውጤት እንደማይለኩት ጠቁመው ትናንት የሊጉ መሪዎች ሲሸነፉ ማየታቸው ትምህርት እንደሰጣቸው ተናግረዋል። አሰልጣኝ ካሳዬ አራጌ በበኩላቸው እረፍቱ ከሥነልቦናዊ ጫና ለቡድናቸው የመተንፈሻ ጊዜ እንደሰጠው አንስተው ውጤቱ ለሀለቱም ቡድኖች አስፈላጊ መሆኑን እና እንደሁል ጊዜው የራሳቸውን አካሄድ እንደሚከተሉ ተናግረዋል።
ይህንን ጨዋታ ፌዴራል ዋና ዳኛ አዳነ ወርቁ በአልቢትርነት የሚመሩት ሲሆን ቡድኖቹም ለጨዋታው ይዘዋቸው ወደ ሜዳ የሚገቧቸው የመጀመሪያ ተጫዋቾች ዝርዝር የሚከተለው ነው።
ወላይታ ድቻ
99 ፅዮን መርዕድ
12 ደጉ ደበበ
4 በረከት ወልደዮሐንስ
9 ያሬድ ዳዊት
8 እድሪስ ሰዒድ
25 ንጋቱ ገብረስላሴ
20 ሐብታሙ ንጉሴ
16 አናጋው ባደግ
21 ቃልኪዳን ዘላለም
11 ምንይሉ ወንድሙ
10 ስንታየሁ መንግስቱ
ኢትዮጵያ ቡና
99 አቤል ማሞ
17 ሥዩም ተስፋዬ
4 ወንድሜነህ ደረጄ
2 አበበ ጥላሁን
11 አስራት ቱንጆ
8 አማኑኤል ዮሐንስ
5 ታፈሰ ሰለሞን
13 ዊልያም ሰለሞን
10 አቡበከር ናስር
21 አላዛር ሺመልስ
16 እንዳለ ደባልቄ