የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ እጣ ድልድል ላይ ያልተካተቱ 7 ክለቦች ዛሬ ክለቦቹ እና ከዚህ ቀደም እጣ የወጣላቸው ክለብ ተወካዮች በታዛቢነት በተገኙበት ይከናወናል።
ባሳለፍነው ሳምንት አጋማሽ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በበላይነት የሚያስተዳድረውን ሁለተኛውን የሊግ እርከን ውድድር እጣ እንዳወጣ ይታወሳል። በስነ-ስርዓቱ ላይ 23 ክለቦች የሚጠበቅባቸውን ክፍያ በወቅቱ በመፈፀማቸው ድልድል ውስጥ ሲካተቱ 7 ቡድኖች ማለትም ጋሞ ጨንቻ፣ አቃቂ ቃሊቲ፣ ወላይታ ሶዶ፣ ከንባታ ሺንሺቾ፣ አርሲ ነገሌ፣ ኮልፌ ቀራኒዮ እና ጅማ አባቡና ባለመክፈላቸው ሳይካተቱ ቀርተው ነበር።
ከላይ የተጠቀሱት ሰባቱ ክለቦች ክፍያ መፈፀማቸው በመረጋገጡ በዛሬው ዕለት (8 ሰዓት ላይ) በፌዴሬሽኑ አዳራሽ የማሟያ እጣ ተከናውኖ ክለቦቹ ምድባቸውን እንደሚያውቁ ለማወቅ ችለናል። እጣው ከሚወጣላቸው ክለቦች ውጪ ሌሎች ክለቦችም በታዛቢነት መገኘት እንደሚችሉ ፌዴሬሽኑ ለሶከር ኢትዮጵያ ገልጿል።
ለማስታወስ ያህል ባለፈው ሳምንት የወጣው ድልድል ይህንን ይመስል ነበር
ምድብ ሀ
ገላን ከተማ
አምቦ ከተማ
ኢትዮ ኤሌክትሪክ
ሻሸመኔ ከተማ
ሀላባ ከተማ
ጌዲዮ ዲላ
ባቱ ከተማ
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ምድብ ለ
ስልጤ ወራቤ
ለገጣፎ ለገዳዲ
ቡታጅራ ከተማ
ከፋ ቡና
ቤንች ማጂ ቡና
ቡራዩ ከተማ
ቂርቆስ ክ/ከተማ
ሰንዳፋ በኬ ከተማ
ምድብ ሐ
ሀምበርቾ ዱራሜ
ፌደራል ፖሊስ
ኢትዮጵያ መድን
ነቀምት ከተማ
ጉለሌ ክ/ከተማ
የካ ክፍለ ከተማ
ደቡብ ፖሊስ