አርባምንጭ ከተማ ለረጅም ደቂቃዎች ሲመራ ቆይቶ አዳማዎች በመጨረሻ ደቂቃ ባስቆጠሩት ጎል አንድ አቻ ከተጠናቀቀው ጨዋታ በኋላ የሁለቱ ቡድኖች አሰልጣኞች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
መሳይ ተፈሪ – አርባምንጭ
ቡድኑ ስላገኘው የአቻ ውጤት?
ያገባነውን ጎል ለማስጠበቅ ብለን አይደለም የተጫወትነው። በዳኛ ሁሉንም ነገር ማሳበብ ተገቢ አይደለም። እኛም ሁለተኛ ግብ የምናገኝበትን ዕድል አተናል። ግን ተመሳሳይ ጥፋቶች እየተሰሩ እኛ ላይ የሚነፉብን ነገሮች አሉ። አንዳንዴ ደግሞ ጥያቄ ስንጠይቅ የሚመለከተው አካል ተገቢውን ጥያቄ መመልከት አለበት። ከፋሲል ጋር በነበረው ጨዋታ የእኛ ተጫዋች ቀይ ሲያይ ምንም ውስጥ አልነበረም ነበር። አሁን ጥሩ ጊዜ ነው። ቪዲዮውን አይተው ሊመልሱልን ይገባ ነበር። እዩልን ብለን ጠይቀን አልታየልንም። አንድ ጥሩን ተጫዋች ሦስት ጨዋታ ማጣት በጣም ነው የሚጎዳው። አሁን ጥሩ ጊዜ ነው። ግን የሚመራው አካል ስህተቶችን ወዲያው ማረም ባይችል ቀስ ብሎ አይቶ ማረም ይችል ነበር። ነገሮች ሲደጋገሙ ነው ቆጣ የሚጨምረው። ተመሳሳይ ጥፋቶችን እናያለን። በተደጋጋሚ ሳጥን አካባቢ ፋውል የሚሰጥብህ ከሆነ ትጎዳለህ።
ግቡ ላይ የነበረህ ቅሬታ?
ውጡቱን ቀይሮታል። ተገቢ የሆነ ቅጣት አይደለም። እሱ ኳስ ብቻ ሳይሆን ተደጋጋሚ ሳጥን አካባቢ ይሰጥ ነበር። ውጤት የሚቀይሩ እንደ ፍፁም ቅጣት ምት እና ኦፍሳይድ ጎል ብቻ አደለም እንደዚህም አይነት ነገሮች ይጎዳሉ። እርግጥ እኛም የምንሰራቸው ጥፋቶች አሉ። እነሱን መታረም አለብን። ግን ዳኞች ሁሉንም እኩል ማየት አለባቸው። የዛሬ ቁጣዬ በተዳጋጋሚ ከተፈጠሩ ነገሮች ነው። እኛ ግን መታረም ያሉብንን ነገሮች እንወስዳለን። በእንቅስቃሴ ደረጃ የምንሰራቸውን ክፍተቶች እናያለን።
ፋሲል ተካልኝ – አዳማ ከተማ
ስለ ጨዋታው
በመጀመሪያው አጋማሽ በተለይ ጎሉ ከገባብን በኋላ የተወሰነ ደቂቃ ብልጫ ቢወሰድብንም እረፍት እስክንወጣ በትክክለኛው መንገድ ተጫውተናል። በሁለተኛው አጋማሽ በመጨረሻው ደቂቃ ግብ ብናገኝም ጉጉትም ተጨምሮ ለእነሱ በሚመች መልኩ ነበር ስንጫወት የነበረም። ዋናው ነገር ጎል ጎል ከገባብን በኋላ እኩል የምንሆንበትን የግብ ዕድሎች መጠቀም አልቻልንም። ይህ በሁለተኛው አጋማሽ ከምንፈልገው ነገር እንድንወጣ አድርጎናል።
ግብ ስለማስቆጠር ችግራቸው
ከጊዮርጊስ ጋር በነበረው ጨዋታ የተጫዋቾቹን ሥነ-ልቦና ከፍ ለማድረግ ስንሰራ ነበር። አንዳንዴ የምናጠቃበት መንገድ ልክ ካልሆነ እሱን ለማስተካከል እንጥራለን። አሁን ግን በደንብ የተጋጣሚ ሳጥን ውስጥ እየደረስን ነው። ግን እየተጠምን አደለም። እዚህ ላይ ማሻሻል ይጠበቅብናል።
እስካሁን አንድ ጨዋታ ብቻ ስለማሸነፋቸው
ከዚህ የምንወጣበት ጊዜ ቅርብ ነው ብዬ አስባለሁ። እንደሚታየው አንዳንድ ጨዋታዎች ላይ የግብ ቅድሚያ ተወስዶብናል። እነዛን አስመልሰን ነው ለማጥቃት እየሞከርን ያለነው። እስከ መጨረሻው ደቂቃ ድረስ ላለመሸነፍ የምንጫወትበትን መንገድ ብወደውም ግን ያገኘናቸውን እስካላገባን ድረስ ከመሪዎቹ እየራቅን ነው የምንሄደው።
ቡድኑ ስላገኘው የአቻ ውጤት?
ያገባነውን ጎል ለማስጠበቅ ብለን አይደለም የተጫወትነው። በዳኛ ሁሉንም ነገር ማሳበብ ተገቢ አይደለም። እኛም ሁለተኛ ግብ የምናገኝበትን ዕድል አተናል።