በዓለም አቀፋ እግርኳስ አስተዳዳሪ ፊፋ የፀደቀ እና በ2022 የፊፋ ኢንተርናሽናል ዳኞች በመሆን የሚያገለግሉ ኢትዮጵያዊ ዋና እና ረዳት ዳኞች ዝርዝር ታውቋል።
ከኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በ2022 በኢንተርናሽናል ዳኝነት እንዲያገለግሉ ስማቸው ለፊፋ ከተላኩ ዳኞች መካከል 7 የወንድ እና 4 የሴት ዋና ዳኞች እንዲሁም 6 የወንድ እና 4 የሴት ረዳት ዳኞች መስፈርቱን በሟማላት ተቀባይነት ያገኙ ሲሆን ከረዳት ዳኞች ሦስቱ (ሙስጠፋ መኪ፣ አበራ አብርደው እና ዳንኤል ጥበቡ) በኢንተርናሽናል ረዳት ዳኝነት ተቀባይነትን ሳያገኝ ቀርቷል፡፡ በዋና ዳኝነት ከተመረጡት ኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ ባምላክ ተሰማ በቪዲዮ ዳኝነትም እንዲመራ በብቸኝነት ተመርጧል፡፡ በአጠቃላይ በቀጣዩ የውድድር ዘመን 21 ኢንተርናሽናል ዋና እና ረዳት ዳኞች ዓለምአቀፍ ውድድሮች የሚመሩም ይሆናል፡፡
በዝርዝሩ ከተካተቱት ውስጥ አሸብር ሰቦቃ፣ ማኑኤ ወልደፃዲቅ እና ምስጋና ጥላሁን ከ2022 ጀምሮ ከፌዴራል ዳኝነት ወደ ኢንተርናሽናል ዳኝነት የሚያድጉ ይሆናል።
የዳኞች ዝርዝር፡
ዋና ወንድ ዳኞች
1 ባምላክ ተሰማ
2 በላይ ታደሰ
3 አሸብር ሶበቃ
4 ቴዎድሮስ ምትኩ
5 ለማ ንጉሴ
6 ማኑኤ ወልደፃዲቅ
7 ኃይለየሱስ ባዘዘው
ሴት ዋና ዳኞች
1 ሊዲያ ታፈሰ
2 ፀሐይነሽ አበበ
3 ምስጋና ጥላሁን
4 መዳብ ወንድሙ
ረዳት ወንድ ዳኞች
1 ክንዴ ሙሴ
2 ትግል ግዛው
3 ሸዋንግዛው ተባበል
4 ተመስገን ሳሙኤል
5 ፋሲካ የኋላሸት
6 ይበቃል ደሳለኝ
ረዳት ሴት ዳኞች
1 ወይንሸት አበራ
2 ይልፋሸዋ ካሣሁን
3 ብርቱካን ማሞ
4 ወጋየሁ ዘውዱ