ኬኒያዊው የመስመር አጥቂ ከሲዳማ ቡና ጋር በመለያየት በይፋ ለሀገሩ ክለብ ፈረመ፡፡
ሲዳማ ቡናን በያዝነው የውድድር ዓመት መጀመሪያ ከተቀላቀሉ የውጪ ዜግነት ካላቸው ተጫዋቾች መካከል ኬኒያዊው የመስመር አጥቂ ፍራንሲስ ካሀታ አንዱ ነው፡፡
ተጫዋቹ በአንድ ዓመት ውል የታንዛኒያውን ሲምባ ክለብ በመልቀቅ ወደ ኢትዮጵያ ከመጣ በኋላ ለሲዳማ ቡና ፊርማውን በማኖር የኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ በሀዋሳ ሲደረግ አብዛኛዎቹን ጨዋታዎች በተጠባባቂ ወንበር ላይ አሳልፏል።
ፍራንሲስ ካሀታ ከሲዳማ ቡና ጋር ቀሪ የስድስት ወራት ውል የነበረው ቢሆንም በግልፅ የተለያየበት ምክንያት ባይታወቅም ወደ ትውልድ ሀገሩ ኬኒያ ተመልሶ በዛሬው ዕለት ለኬኒያው ፖሊስ ክለብ የአንድ ዓመት ውል መፈረሙን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።