ሻሸመኔ ከተማ የመጀመሪያ ፈራሚውን አግኝቷል

የአሰልጣኝ ፀጋዬ ወንድሙ ሻሸመኔ ከተማ የመስመር አጥቂውን የመጀመሪያ ፈራሚው አድርጓል።

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላይ ከ15 ዓመታት በኋላ በአሰልጣኝ ፀጋዬ ወንድሙ እየተመራ ከከፍተኛ ሊጉ ወደ ፕሪምየር ሊጉ ያደገው ሻሸመኔ ከተማ ከቀናቶች በፊት የአሰልጣኙን ውል ያራዘመ ሲሆን ወደ ዝውውሩ ዘግየት ብሎ በመግባት በዛሬው ዕለት የመጀመሪያ ፈራሚ ተጫዋቹን ስለ ማግኘቱ ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።

እዮብ ገብረማርያም ክለቡን በአንድ ዓመት ውል መቀላቀል የቻለው ተጫዋች ሆኗል። የቀድሞው የኮምቦልቻ እና ገላን ከተማ ተጫዋች ኢትዮጵያ መድንን በ2014 ከተቀላቀለ በኋላ እስከ ተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ድረስ በፕሪምየር ሊጉ ከመድን ጋር ቆይታ የነበረው ሲሆን ለቀጣዩ ዓመት ማረፊያውን ሻሸመኔ አድርጓል።