[iframe src=”https://bbc.com/” width=”1%” height=”1″]
በኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ የሚሳተፈው መከላከያ ለበርካታ ተጫዋቾች የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ሲሰጥ ሁለት ተጫዋቾቹንም ከ20 ዓመት በታች ቡድኑ ጋር ልምምድ እንዲሰሩ ወስኗል።
በአሠልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ የሚመራው መከላከያ በዘንድሮ የውድድር ዓመት ዳግም ወደ ሊጉ ማደጉ ይታወሳል። በ11 ሳምንታት ጨዋታዎችም 14 ነጥቦችን በመሰብሰብ 10ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። በትናንትናው ዕለት ከአምስት ጨዋታዎች በኋላ ከድል ጋር የታረቀው ክለቡ ከጨዋታው በፊት ለዘጠኝ ተጫዋቾች የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ መስጠቱን የዝግጅት ክፍላችን አረጋግጧል። ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸውን ተጫዋቾች ስም ዝርዝር ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ባይሳካም ከ9ኙ ውስጥ አራቱ የመጨረሻ አምስቱ ደግሞ የመጀመሪያ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው አውቀናል።
ከዘጠኙ ተጫዋቾች ውጪ ደግሞ የአማካይ መስመር ተጫዋቹ ዓለምአንተ ካሳ እና የአጥቂ መስመር ተሰላፊው ገዛኸኝ ባልጉዳ ከዋናው ቡድን ወርደው ከ20 ዓመት በታች ቡድን ጋር ልምምድ እንዲሰሩ መወሰኑን አረጋግጠናል።