ከቀናት በኋላ ኢትዮጵያን የምትገጥመው ሴራሊዮን ስብስቧን ይፋ አደረገች።
ለ2026 የአለም ዋንጫ የማጣሪያ ኢትዮጵያ በምትገኝበት ምድብ የተደለደሉት ሴራሊየኖች ከኢትዮጵያ እና ግብፅ ላሉባቸው ሁለት የዓለም ዋንጫ የማጣርያ ጨዋታዎች ቡድናቸውን ይፋ አደርገዋል። ለዓመታት የብሄራዊ ቡድኑ ምክትል አሰልጣኝ ሆነው በመስራት ከወራት በፊት ቡድኑን በዋና አሰልጣኝነት ተረክበው ሁለት የአቋም መፈተሻ ጨዋታዎች ያደረጉት የአርባ ዘጠኝ ዓመቱ አሰልጣኝ አሚዱ ካሪም ለመጀመርያው የነጥብ ጨዋታው በኢንግሊዝ ታችኛው ሊጎች የሚጫወቱ ተጫዋቾችም አካተዋል።
በተጠናቀቀው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ናይጀርያና ጊኒ ቢሳውን ተከትለው በሦስተኛ ደረጃነት በማጠናቀቃቸው ኮትዴቭዋር ለምታዘጋጀው የአፍሪካ ዋንጫ ማለፍ ያልቻሉት ሴራሊየኖች ካከናወኗቸው የመጨረሻ አስራ ሁለት ጨዋታዎች ኬፕ ቨርዴ፣ ሳኦ ቶሜ ፕሪንስፔና ሶማልያ ላይ ድል ሲቀዳጁ፣ በአራት ጨዋታዎች አቻ በአምስቱ ደግሞ ሽንፈት አስተናግደዋል።
ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾች 👇