[iframe src=”https://bbc.com/” width=”1%” height=”1″]
ያለ ጎል ከተጠናቀቀው የምሽቱ ጨዋታ በኋላ አሰልጣኞች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡
አሰልጣኝ ፉአድ የሱፍ – ድሬዳዋ ከተማ
ስለ ጨዋታው ሂደት እና ስለ ሁለተኛው አጋማሽ
“ከእረፍት በኋላ ያው ኳስ ይዘው እንዲጫወቱ ነው ያደረግነው። የተጫዋች ለውጥ አድርገን የተሻለ ከእረፍት በኋላ ይዘን ለመጫወት ሞክረናል፡፡ ነገር ግን ማሸነፍ ነበረብን፤ ባለፈው የጣልነውን ነጥብ ህዝቡን ለመካስ ነበር። ዛሬ ጉሮሮ እስኪሰነጠቅ ሲደግፈን የነበረውን ተመልካች አሸንፈን ለመካስ ነበር፡፡ያ ሳይሆን ቀርቷል። አሁን ቀጣይ እንግዲህ እየሠራን ለማሸነፍ እንዘጋጃለን፡፡
አዲስ አሰልጣኝ በመሆንህ ስለ ተፈጠረ ክፍተት እና ከተጫዋቾች ጋር ስላለህ ትውውቅ
“በቴክኒካል ዳይሬክተር ሆኜ በአብዛኛው ስለምንግባባ እና ልጆቹ ያውቁኛል። አብዛኛው ስራ የሰራነው የቡድን ስራ ላይ ነው፤ ያ ተሳክቶልናል፤ የማሸነፍ ፍላጎት ውስጣቸው እንዲቀረፅ አድርገናል፡፡ እንግዲህ በሂደት የተሻለ ነገር ይዘን እንቀርባለን የሚል ነገር ነው ያለኝ። ተመልካቹ በትዕግስት እንዲጠብቅ ነው የምፈልገው፡፡
የመጀመሪያው አጋማሽ ስለመባከኑ
“በጣም አባክነናል፤ ምክንያቱም እኔ የምፈልገውን ጨዋታ ትተን የነሱን ጨዋታ ነበር ስንጫወት የነበረው። እነርሱ ረጅም ጨዋታን እንደሚጫወቱ እናውቃለን፤ ያን እንዳይጫወቱ ኳስ መስርተን እንድንጫወት ነበር ስላቸው የነበረው። ያን ግን ተግባራዊ ሲያደርጉ አልነበረም። ከዛ ባደረግነው ለውጥ መሠረት የተሻለ ነገር ከእረፍት በኋላ ልናደርግ ችለናል፤ ረክቻለሁ፡፡
አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ – አርባምንጭ ከተማ
ስለ መጀመሪያው አጋማሽ ጥንካሬ እና ስለ ሁለተኛው አጋማሽ መዳከም
“መጀመሪያ ላይ ስህተቶች ነበሩ። ሁለተኛ አርባ አምስት ላይ እነሱ ቶሎ ቶሎ ከሜዳ እየወጡ ተፅእኖ ለማድረግ ጥረት ሲያደርጉ ነበር፡፡ እንዳልከው የመጀመሪያው አርባ አምስት የተሻለ እንቅስቃሴ ስናደርግ ነበር። ሁለተኛው አርባ አምስት እነርሱ ከእኛ የተሻሉ ናቸው፡፡ ኳሶችን ቶሎ ብለን ከሜዳ እየወጣን እነርሱ ፕረስ አድርገው አጥቂ አብዝተው ቀጥተኛ ኳስ ለመጠቀም ጥረት ሲያደርጉ ነበር፡፡ ስለዚህ ይሄን አይተናል በመጀመሪያ እና በሁለተኛው፡፡
ስለ ኬንያው ተከላካይ በርናንድ አቼንግ ቀይ ካርድ እና ስለ ዳኝነቱ
“እንግዲህ ሀላፊነቱ የእነርሱ ነው፤ ያዩታል ብዬ አስባለሁ፡፡
ስለ አጨራረስ ክፍተት
“ባለፈው አስቆጥረናል፡፡ አንድ ጎል አግብተናል። ዛሬ የተለያዩ የጎል አጋጣሚዎችን ፈጥረናል፤ አንዱ ጠንካራ ነገር በእግር ኳሱ ውስጥ ወደ ጎል መድረስ መቻል ነው፡፡ አጋጣሚዎችን መፍጠር ነው። ብዙ አጋጣሚዎችን እየፈጠርክ ከዛ ወደ ማስቆጠሩ ትመጣለህ። ግን በተለይ በመጀመሪያው አጋማሽ እንገባባቸው የነበሩ ጠንካራ ማጥቃቶች ነበሩ። ባለፈውም ጎል አስቆጥረናል። በቀጣይ እነዚህን ችግሮች እየቀረፍን እንሄዳለን፡፡
ተጫዋቾች በተደጋጋሚ ስለሚያዩት ካርድ
“የባለፈው ተገቢ ነው፡፡ አሁን እንግዲህ ምናልባት ቪዲዮዎቹን ማየት ጥሩ ነው የሚሆነው። የእኛ ልጆችን እንዲታረሙ ማድረግ መታየት ያለባቸው ነገሮች ካሉ በተለይ የቆሙ ኳሶች ላይ ሊያጣሉ የሚችሉ ነገሮች እነርሱ ናቸው የነበሩት። እነዚህን በደንብ አድርጎ ማየት ነው፡፡ ለህግ መገዛት ተገቢ ነው ያንን እናደርጋለን፡፡
ስለ ቀጣይ መሻሻሎች
“ጠንካራ ነገሮች አለን። እንደዚሁ ዝም ተብሎ በነሲብ አልመጣንም፤ ምንሰራውን እናውቃለን ድክመታችንን እናውቃለን፡፡ ስለዚህ ምንም ጥያቄ የለውም እንታረማለን፡፡ በቀጣይ እያሸነፍን እየሄድን መሻሻላችን አይቀርም ግድ ነው፡፡