የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከረጅም ትራንዚት በኋላ የአልጀርስ ጉዞውን ጀምሯል

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከአልጄርያ ጋር ለሚያደርገው የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ማጣርያ ጨዋታ 28 የልኡካን ቡድን በመያዝ ትላንት ምሽት 04:45 ላይ በረራ ጀምሯል፡፡ ቡድኑ በአጭር በረራ ግብፅ ካይሮ 6:00 ገደማ ከደረሰ በኋላ እስከ ንጋት ድረስ ረጅም ትራንዚት ለማሳለፍ ተገዷል፡፡ ሰአቱ 2:40 ገደማ ሲሆን ወደ አልጀርስ ጉዞ ጀምረዋል፡፡ የልኡካን ቡድኑ በኛ ሰአት አቆጣጠር 07:00 አልጀርስ እንደሚደርስ ሲጠበቅ ጨዋታው ወደሚደረግበት ቢልዳ ከተማ የ45 ኪ/ሜ የመኪና መንገድ በመጓዝ ወደተዘጋጀላቸው ሆቴል ያመራሉ፡፡

PicsArt_1458629846704

በፎቶዎቹ ላይ እንደሚታዩት ተጫዋቾቹ በካይሮ አየር ማረፍያ የመንገደኞች ማስተናገጃ ውስጥ በመተኛት ያሳለፉ ሲሆን የአብይ ፆም የሚፆሙ ተጫዋቾችም የፆም ምግብ ለማግኘት ሲቸገሩ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡ ከቡድኑ ተሰላፊዎች መካከል አራቱ የቅዱስ ጊዮርጊስ ተጫዋቾች በጉዞው እጅግ ሳይዳከሙ አልቀሩም፡፡ ከቲፒ ማዜምቤ ከተደረገው ጨዋታ በኋላ ሰኞ ጠዋት ከኮንጎ ተነስተው ምሽት 2:00 አዲስ አበባ የገቡት አሉላ ፣ አስቻለው ፣ ራምኬል እና በሃይሉ በቂ እረፍት ሳያደርጉ ከብሄራዊ ቡድኑ ጋር ሌላ ጉዞ ጀምረዋል፡፡

PicsArt_1458629909999

“የጉዞው ነገር እጅግ አድካሚ እንደሚሆን እናስባለን፡፡ የሁለት ቀን መንገድ ነው፡፡ ረጅም የጉዞ ፕሮግራም እንደመሆኑ የጉዞ መዘግየት እና ተያያዥ ምክንያቶች ሊኖሩ ስለሚችሉ እኛም ቀደም ብለን ጉዞዋችንን ጨዋታው ከሚደረግበት ቀን አራት ቀናት አስቀድመን ወደ ስፍራው ለመሄድ ወስነናል፡፡ ከቡድኑ ተጨዋቾች ጉዞውን ከባድ የሚያደርገው ከቅዱስ ጊዮርጊስ ለተመረጡት ተጨዋቾች ነው፡፡ ለክለባቸው በአፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ ወደ ኮንጎ ማምራታቸውን ተከትሎ አዲስ አበባ ላይ ምንም ልምምድ ሳያደርጉ እዛው አውሮፕላን ማረፊያ ቡድኑን ተቀላቅለው ረጅም ጉዞ ያደርጋሉ፡፡ ” ሲሉ አሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌከጉዞ ጋር በተያያዘ በትላንቱ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ መናገራቸው የሚታወስ ነው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *